Selam guys sleep andbirru santim yemiweraw ewnet new?? Arat bale ge'ez digit yalew santim yishetal mnamn mibalew?
Dec 12, 2022#ተጠንቀቁ • " የአንድ ብሩን ሳንቲም በሺዎች በሚቆጠር ገንዘብ እንገዛለን ከሚሉ አጭበርባሪዎች ራሳችሁን ጠብቁ " - ብሄራዊ ባንክ • " ድርጊቱ በህግ የሚያስጠይቅ ነው " - ፖሊስ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ " የአንድ ብሩን ሳንቲም በሺዎች በሚቆጠር ገንዘብ እንገዛለን " ከሚሉ አጭበርባሪዎች ኅብረተሰቡ ራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጠው ቃል ፤ ከሰሞኑ በተለያዩ ማኅበራዊ ድረገፆች " አራት የግዕዝ ፊደላት ያሉትን የአንድ ብር ሳንቲም በ2 ሺህ ብር እና ከዚያም በላይ እንገዛለን " የሚሉ ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ ማስታወቂያዎች በስፋት ተስተውለዋል ብሏል። ማስታወቂያዎቹ ኅብረተሰቡን ለማጭበርበር እየተነገሩ ያሉ እና ከእውነት የራቁ በመሆናቸው ፤ ኅብረተሰቡ ራሱን ከአጭበርባሪዎች ሊጠብቅ እንደሚገባ ገልጿል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ በበኩሉ፣ ድርጊቱ በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን ገልጾ በዚህ ማጭበርበር ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ግለሰቦች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ ማስጠንቀቁን ቴሌቪዥን ጣቢያው ዘግቧል። @tikvahethiopia
Dec 12, 2022