ሰላም የመጠጥ ሱስ ነበረብኝ እና ለማቆም ብዙ ጊዜ ሞክሬ አልተሳካም...እና ባለፈው ሳምንት በእናቴ ማልኩኝ ማለት በጣም ስለምወዳት ከአሁን በኋላ ከጠጣሁ ፈጣሪ እናቴን ንሳኝ ብዬ ግን በሳምንቱ ተመለስኩኝ አሁን እናቴ በጣም ታማ ሆስፒታል ነው ያለችው አስቡት የሷ ህመም አለ plus በኔ ምክንያት ነው እንደዚህ የሆነችው ብዬ ትልቅ የማልወጣው ፀፀት ወስጥ ነኝ እና ጥያቄዬ እውነት የማልኩት ደርሶ ነው ወይስ በአጋጣሚ የሆነ ነገር ነው ብላችሁ ታስባላችሁ እስኪ ሀሳበችሁን ስጡኝ ???
Dec 10, 2022እናትህን ፈጣሪ ይማርልህ እናቶች መታመም የለባቸውም ረጅም እድሜ ለሁሉም እናቶች 🙏 ማወቅ ያለብህ የሚሆነው ሁሉ ፈጣሪ ስላለው ነው አንተ እንደዛ ባትልም ልትታመም ይችል ይሆናል ሁሉን የሚያውቀው ጥበበኛው ፈጣሪ ብቻ ነው 🤷♂ ካንተ የሚጠበቀው እናትህን በደንብ አስታምማቸው ተንከባከባቸው ሌላውን ለፈጣሪ ተወው ደሞ የመጠጡንም ነገር አደራ 😔 በድጋሚ እናትህን ፈጣሪ ይማርልክ 🙏
Dec 11, 2022