Erasen be melka ke sew ga ymantsatser chger albgn ena eytgodahu new endet kezi aynt semt lwta
Dec 09, 2022"""" ወንድ ከሆንክ ውበት ያን ያህል ሊያሳስብህ አይገባም!!!..... ሴት ከሆንሽ ደሞ ውጫዊ ውበትሽ በሰዎች ላይም ሆነ በራስሽ ላይ የሚፈጥረው ተፅእኖ ከፍተኛ የሚባል ነው ለሞራልሽ አስቤ ላሞኝሽ አልፈልግም ግን የምመክርሽ ነገር ቢኖር ሰዎች ለራስሽ የምሰጪውን ቦታ አይተው ነው የሚያከብሩሽ የሚንቁሽ እና ሌላም ሌላም ስላንቺ የሚስማቸው ያው ባለቤቱ ያቀለለውን ባለዳ አይቀበለውም አደል ተረቱስ😉.... ያማለት እንሱ የሚሰማቸው ነገር በሙሉ የራስሽ እጅ አለበት!!....እና በአጭሩ ለራስሽ ያለሽን አመለካከት ቀይሪ ከሰዎች ጋር ያለሽንም ተግባቦት በመጠኑ አሳድጊ የሚንቁሽን ሰዎች ገደል እንዲገቡ ምከሪያቸው👉...ደሞ ያን ያህል አስቀያሚ የምትባይ አደለሽም እርግጠኛ ነኝ! ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ቁንጅና አለው ውስጣዊ ውበት ምናምን እያልኩ አላጃጅልሽም ነገር ግን ምንም እንኳን ቆንጆ ባይሆኑም ባህሪያቸው አሪፍ እና ተጫዋች የሆኑ ሰዎች በቀላሉ ሰዎችን እንደሚስቡ እንዲሁ ከህይወት ልምድሽ መረዳት የሚከብድሽ አይመስለኝም 🤷♂ ...ስለዚ አሁን ምን እያልኩሽ እንደሆነ እየገባሽ ይመስለኛል ስለማይቀየረው ውጫዊ ውበትሽ ማሰቡን ትተሽ በትንሽ ጥረት እና ልምምድ ስለምቀይሪው ወስጣዊ ውበትሽ(ውስጣዊ ውበት ከምንለው ባህሪ እንበለው!) አስቢ!!!😊 ደሞ ሰዎች ምንም ቢሉሽ በራስሽ ላይ ያለሽን አመለካከት እንዲሸረሽር እንዳታረጊ አደራ !✋ሰዎ አምሮብሽላ እስካላለሽ ድረስ እንዳላማረብሽ ካሰብሽ በቃ ተበልተሻል😁....ደስታሽን በሰዎች እጅ ላይ በፍፁም እንዳታረጊ!!!!! መልካም ዘመን አስጠሊዋ✋😐" " የሆነ ጊዜ ላይ ከዚህ ጥያቄ ጋር ለሚመሳሰል ጥያቄ የሰጠሁት ምላሽ ነው! ...ልጁ ይህን ካልኩት በኋላ በጣም ደስ ተሰኝቶ ነበር ላንተም እንደሚጠቅምህ ተስፍ አለኝ😊🙏
Dec 09, 2022