ሰላም guys 2 ጥያቄዎች ነበሩኝ 1. አንድ ሰው 666 ውስጥ ቢገባ እና የ illuminate አባል ቢሆን ብዙ ጥቅም ቢያገኝ እና life ቢቀይር እዛ ውስጥ ሆኖ ብዙ ጥፋቶችም ሆነ ጥቅሞች ቢያገኝ ከዚህ ሁሉ የጥፋት መንገድ ይህ ሰው መዳን እና ከዚ ነገር መውጣት ቢፈልግ የእየሱስ ደም ከዚ እስራት ነፃ ሊያወጣው ይችላል ማለት ሲገባ ቃል ኪዳን አድርጎ ነፍሱን ስለሸጠ ሰይጣን ለመውጣት ሲጥር የሚያጠፋው ይመስላችኋል ወይስ መዳን ይችላል??? 2. እራስን ያጠፋ ሰው የዘላለም ህይወት ያገኛል ማለት ሁሉም ሀጢያት እኩል ነው ሀጢአት ደሞ ከድህነት አያስቀርም በክርስቶስ ላመነ ሰው ስለዚህ በእየሱስ አምኖ የዳነ ሰው እራሱን ቢያጠፋ መንግስተ ሰማያት ይወርሳል ወይስ አይወርስም። Tnx 4 ur answer
Dec 06, 20221) ወደ አምልኮተ ሰይጣን የሄደ ሰው ቢመለስ ቄደር ተደርጎለት ንሰሐውን ተቀብሎ መዳን ይችላል። ይሄንን የማድረግ እድሉ ግን ሲበዛ በጣም ጠባብ ነው። ምክንያቱም የሰይጣን ቤት ለሥጋ ይጣፍጣል፥ የምትፈልገውን ነገር ሁሉ ታገኛለህ፣ እውቅናን ገንዘብን ደስታን ተድላን ታተርፋለህ። ከዚ ምቾት መውጣት በጣም ከባድ ነው። እሱን ተወጥቼ እተወዋለሁ ብትል እንኳ ሕይወትህ አዳጋች ሁኔታ ውስጥ ሊገባ ይችላል። ግን እሱ ብዙም አያስጨንቅም፥ ነፍስህ ከዳነ በሥጋ መሞት መቼስ አይቀሬ ነው። 2)ሁሉም ኃጢአት እኩል አይደለም። ጽድቅም ኃጢአትም ልክ እንደሰማይ ከዋክብት ይበላለጣሉ። ህጻናትን የፈጀው የሔሮድስ በደል እና ፈርቶ የዋሸው የጴጥሮስ ኃጢአት በሰማይ ቤት እኩል አይደለም። ነፍሰ ገዳይ መንግሥተ ሰማያትን የማይወርስ እንደመሆኑ እራሱን የገደለ እንዲሁ ጉዱ ነው።
Dec 06, 2022