ሰላም ቤተሰቦች በህልሜ አንበሳ ሲያባርረኝ ነበር እና ፍቺው ምን ይመስላችሁዋል ሳትቀልዱ please
Dec 04, 2022"Temple Run" game መጫወት ታበዛለህ እንዴ¡ ወደ ቁም ነገሩ እንሂድ።👇 አንዳንዴ በቀን ዉሏችን ያደረግነው፣ የሰማነው፣ ያየነው ወይም ያሰብነው ነገር በተኛንበት የመከሰት ነገር አለ። አንተም ተኝተህ ይህን ህልም ከማየትህ በፊት ስለ አንበሳ አስበህ፣ አይተህ ወይም ሰምተህ ከነበር ነገሩ ህልም ሳይሆን ቅዠት በመሆኑ ምንም ትኩረት አትስጠው፣ እርሳው። ያ ካልሆነ ግን ቀጣዩን አንብብ። እንደ ጾታና የትዳር ሁኔታ ፍቺው ቢለያይም ጠቅለል ያሉ ፍቺዎቹ የሚከተሉት ናቸው ከጥሩ ፍቺው ልጀምር 1, አንበሳው አንተን አለመጉዳቱ ነው። ይህም ከሚመጣብህ መጥፎ ነገር የማምለጥ እድል እንዳለህ ነው። ከፍርሃት፣ ጭንቀት፣ ሃዘንና አንተን ሊጎዱ ከሚችሉ አካላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ነገሮች የምትድን ትሆናለህ። 2, ፊት ለፊትህ አለመቆሙ: እንዲያ ከሆነ በቅርበት የምታውቀው ሰው ይህችን ዓለም ሊሰናበት እንደሆነ ያመላክታል። (አያድርግብህ!) ጥሩ የማይባል ፍቺው 1, ወዳጅህ ያልሆነ ውድቀትህን የሚፈልግ ተንኮል የሚያሴርብህ ጠላት መኖሩ ሲሆን ይህን ለመከላከል ራስህንም ማዘጋጀት እንዳለብህ ይነግርሃል። 2, ጊዜያዊ ቢሆንም ደስታህን የሚያጨልም ሃዘን እየመጣ መሆኑ ነው። በተረፈ ለመጥፎው ተዘጋጅ፣ ለደጉም ተዘጋጅ። ፈጣሪህን ከክፉ እንዲጠብቅህና መልካሙን እንዲገጥምህ ለምነው።
Dec 05, 2022