ሰላም ሰዎች ✋ ደግሞ መጣሁ አንድ ሰው ከአምላኩ ፍቅር ሊይዘው ይችላል እንዴ ? በቃ አምላኩን ብቻ እያሰበ እሱ ያዘዘውን ብቻ እያደረገ አምላኩን ከልቡ እያፈቀረ መኖር ይችላል ?
Dec 04, 2022አዎ ይችላል !! መገለጫው ግን ልዩ ልዩ ነው። በዓለም ውስጥ ሆነው ይኽን የፈጸሙ አሉ በምናኔ ሕይወትም እንዲሁ ይኽን የፈጸሙ አሉ እየፈጸሙም ያሉ አሉ። አንድ ልጅ የሰው ልጅ አምላኩን ሊያፈቅር አይችልም ቢችል ኖሮ ቀን እና ማታ 24 ሰአት ያለቅስ ነበር ሲል የመለሰውን ተመልክቼ ነበር ቅዱስ ዮሐንስ በአንደኛው መልዕክቱ እንዲ ይለናል ፍቅርም እንደዚ ነው እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደወደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስርያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደወደድነው አይደለም" ይኽን ሲል ሐዋርያው እኛ ምንም ያኽል እግዚአብሔርን ብንወደው ወይም ብናፈቅረው እኛ ለሱ ያለን ፍቅር እሱ ለኛ ያለውን ካለው ፍቅር ቅንጣቷን አትሆንም(ለዚኽም ነው መበደላችን ሳይሆን ንስሀ አለመግባታችን ይበልጥ እግዚአብሔርን የሚያሳዝነው) የሆነ ሆኖ 24 ሰአት ሲያለቅሱ የኖሩም አሉ ጥቂቶቹን እንደ ምሳሌ ለማንሳት ያኽል ቅዱስ አርሳኒዮፈዎስ:-ከለቅሶው ብዛት የተነሳ የዓይኑ ጭራ ሰብሮ ቀጉንጮቹ ሚወርድበት ቦይ ፈጥሯል።በክርምት ወቅት የዘንባባ ዝንጣፊ አንጥፎ እንባው የሚፈስበት ጨርቅ ዝንጣፊው ላይ አስቀምጦ ይተኛ ነበር። ይህ ቅዱስ አባት በአርምሞ/በዝምታ/ ህይወትም አርዓያ ተደርጎ ይወሰዳል። ኢሳዶር:-ይህን አባት ሰይጣን እጅጉን ይፈራው ነበር።አንድ ቀን ሰይጣን ተገለጠ እና ''አይበቃህም እንዴ እንኳን በአንተ በአት በጎረቤቶችህ በአት አጠገብ ማለፍ አልቻልንም'' ይህ አባት ግን ያለቅስ ነበር። መቃሪዎስ. .ፓፒኑቶየስ. .አባ ጴሜን. .አቡነ አቢብ(ቡላ) ብዙ መዘርዘር ይቻላል።
Dec 05, 2022