Do you think there is real love between human beings?
Dec 03, 2022Nope according to my definition of love. For me to experience true love you have to kill your ego which is impossible unless you're somewhat a supernatural being. ፍቅርን ፈራን.... ፀጋዬ ገብረመድህን ይላል በግጥሙ ፍቅር እውነትም አስፈሪ ነው የምንፈራው ፍቅርን ሳይሆን ግን ራስን ማጣት ነው (ego)። ፍቅር በነፃነት ያምናል, ፍቅር እራስን አሳልፎ መስጠት እንጂ ሌላን ግለሰብ መቆጣጠር ማለት አይደለም(Ownership)። ፍቅርን logic (አመክንዮ) ትርጉም ሊሰጠውም ሆነ ሊረዳው አይችልም ምክንያቱም የፍቅር ምንጩ ልብ እንጂ አእምሮ አይደለም። ፍቅር አንደኛውን ልክ ሌላኛውን ስህተት አያደርግም በፍቅር ውስጥ ሁሉም ልክ ነው። ፍቅር ቅድመ ሁኔታ አያስቀምጥም እውነተኛ አፍቃሪም ያለ ቅድመ ሁኔታ ያፈቅራል። አእምሮህ ለፍቅር እንቅፋት ነው ምክንያቱም ምንግዜም አእምሮህ እኔ እንዴት ልጠቀም እንጂ ለሌላው ራስን አሳልፎ መስጠት ሊነግርህ አይችልም። የፍቅር ምንጩ ልብ ነው አእምሮ ግን የፍርሃት ምንጭ ነው። መፅሐፍ እንደሚል “በፍቅር ፍርሀት የለም፤ ፍጹም ፍቅር ግን ፍርሀትን አውጥቶ ይጥላል፤ ፍርሀት ከቅጣት ጋር የተያያዘ ነውና። የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።” ፍርሃት የፍቅር ተቃራኒ ነው። ልብ ፍርሃትን አያውቅም አእምሮህ ግን ፈሪ ነው። አንድ ጠቢብ ሰው ምን አለ ፈሪ ሰው አእምሮውን በጣም የሚጠቀም ሰው ነው ይላል። ልክ ነው አሁን ሳስበው አለም ለፍቅር ቦታ የላትም በአለም ለመኖር ምንግዜም ንቃት እና ብልጠት ያስፈልጋል። ያለ ቅድመ ሁኔታ ማፍቀር ስንችል ከአእምሮ ሳይሆን ያኔ ከልባችን ማፍቀር እንጀምራለን። አፍቃሪ ሰው ጥበበኛ ነው ሲበዛም ደፋር ነው። ያፈቀረ ሰው ምን ሊያስፈራው ይችላል? ከፍቅር ጋር ማነው የሚስተካከል? እግዚአብሔር ፍቅር ነው ይላል መፅሐፍ። ልክ ነው አምላክ ፍቅር ካልሆነ ምንም ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ፍቅርን የሚበልጥ ምንም ነገር ስለሌለ።
Dec 03, 2022