ሠላም ክርስቲያኖች እባካችሁ ስለ ሳምራዊቷ ሴት ወይም 7 አጋንንት ስለወጣላት ሴት ወይም 12 ዓመት ደም ይፈሳት ስለነበረችው ሴት ወይም በዝሙት ስለነበረችው ጌታን ሽቱ ስለቀባችው ሴት ወይም ደግሞ ስለ መፃጉ... ብቻ የሆነ ክርስቶስ ሳይፀየፍ ታሪካቸውን ስለቀየረላቸው ሰዎች የሚያወራ ግጥም ወይም መነባንብ ካላችሁ ላኩልኝ 🙏🙏🙏
Dec 03, 2022መጻጉ የቱ ፍቅሬ ስቦህ እንደምን ፈታኸኝ እኔ እኮ ብኩን ነኝ... አንተ ስትሰቀል ከአይሁድ ጋር የምገኝ እኔ እኮ ምንም ነኝ ተራ የህመም ሰው ጌታ እንድትምረኝ ምክንያትህ ምንድነው በከሀሊነትህ ቢቆምም የኔ አሳር ከደግነት ደጅህ የቆረጥኩኝ ምሳር ብትወደኝ ብትምረኝ እኔ ምንተዳዬ ከሰቀሉህ ጋራ ልስቀልህ ጌታዬ እንዲ ነኝ መጻጉ ውለታ የምረሳ ስወድህ እንድኖር ህመሜን አትፈውስ ቀንበሬን አታንሳ ስንኩል ነው የኔ እግሬ ለሐሰት ያጋደለ ጠማማ ነው ልቤ ፍቅርህን የጣለ ቀጤማ ነው እጄ ክፋት ያቃጠለው ያዙት ያን ክርስቶስ ብሎ የሚጠቁመው እውር ነው ብሌኔ እያየ የሚከዳ ከደግነት ኩሬ መአት የሚቀዳ እዳ ነኝ ለራሴ እዳ ነኝ ለዓለም ሲጀመር ነው የካድኩህ ሲፈጸም አይደለም ከወንዙ ጥግ ሆኜ በአልጋዬ ላይ ሳለሁ አምንብህ ነበረ ሲትፈውስ እያየሁ አልጋህን ተሸከም ስትለኝ ምን አልባት ልቤን አናተበው የመራመድ ክፋት አትማረኝ መድህኑ በአልጋዬ ላይ ልክረም አልጋዬን መሸከም ለኔ መጥፋት እንጂ መፈወስ አይደለም እባክህ ክርስቶስ እባክህ ጌታዬ አንተን ከምከዳ አልጋዬን አዝዬ የዳዊት ልጅ ተወኝ አትፈውሰኝ ይቅር መች እወድህ ነበር ይህ ሁሉ ካልነበር::
Dec 04, 2022