My mom hates me she hates me so much i don't know what i did wrong all i ever wanted to do is make her happy which never worked betam geltse yehone madalat new beka ebet west yalew wendemen enji ene sew meseyem aletayatem madergew ngr bemulu aytematem enkuan tefat atfeche salatefa enkuan enen metekotabet mekeniyat new metefelegew mn adregeyat endehone alawekem bzu gize tefi tefi new milegn be esua mekeniyat bzu alkeshalew mn madreg endalbegn alawekem
Nov 30, 2022እኔ በአካባቢዬ የማውቃት እናት አለች። ልክ እንዲሁ ሁለት የመጀመሪያ ሴት ልጆቿን የምትበድል። ሀብታም ናቸው፣ ቤት ውስጥ 5 ሰራተኛ አላቸው። ነገር ግን እነዚያን ሰራተኞች አስቀምጣ ልጆቿን ወንድ የማይሰራውን ሁሉንም የቤት ስራ ታሰራቸው ነበር። ሰላይ ቀጥራ ታጨናንቃቸው ነበር። እሷና ባሏ መጀመሪያ በስራ ውጭ አገር ነበሩ። እዛው ወልደዋቸው እዚህ አምጥተው ለዘመድ ሰጥተው ነበር ለ9 አመት ያደጉት። ኋላ ወላጆች ወደ አገር ተመልሰው ልጆቹን ተረክበው በትክክል ማሳደግ አልቻሉም። ሴቶቹም ለእናታቸው አንገት ደፍተው ሰርተው ኖሩና ጊዜያቸው ሲደርስ ፈጣሪ በትዳር ባርኳቸው አግብተው ወጥተው ተገላገሏት። ይህን የምነግርሽ ብቸኛ እንዳልሆንሽ እንድታውቂ ነው። 1, አንዳንድ ሞኝ እናቶች ሴት ልጆቻቸው አደግ ሲሉላቸው ፈጣሪን ከማመስገን ይልቅ ቅናት ያድርባቸዋል። ጭራሽ ባሏን/አባትሽን ልትቀሚያቸው ነው የሚመስላቸው። በዚህም ሴት ልጇን ትበድላለች። 2, ሌላው ደግሞ እስካሁን ከሰው ባልሰማውም እናት ተብዬዋ ሴትም ትሁን ወንድ ልጇን እንዲህ እንድትበድል የሚያደርጋት ምን እንደሆነ ትኩረት ሰጥቼ ሳስበው (ሰይጣን የነገረኝ ይመስለኛል) በድብቅ ባል ሳያውቅ ከሌላ ጎረምሳ የወለደቻት/የወለደችው ልጅ መሆኑን ካወቀች ያ ልጅ በዚህም በዚያም ብሎ እንዲጠፋ/እንዲሞት የምታደርግ ነው የሚመስለኝ።🤷🏽♂ 3, አንዳንድ ሴቶች የድሮ ማንነታቸው የዘቀጠ ስለነበር የወለዷትም ሴት እንደርሷው የሆነች የሚመስላቸውም ይኖራሉ።🤷🏽♂ ለሁሉም መታገስ አይከፋም። አንዳንድ እናቶች እናትነታቸው የስም ብቻ ነው። አንቺም ለአቅመ ሔዋን የደረስሽ ትመስያለሽ። ስለዚህ እያንዳንዱ እርምጃሽ በብስለትና በትዕግስት የተሞላ መሆን አለበት። እናትሽ ሆን ብላ ልታበሳጭሽና በአባትሽ/በዘመድ/በኅብረተሰቡ አይን መጥፎ እይታ እንዲይዙብሽ ማድረግ ትፈልግ ይሆናል። ታድያ ትዕግስት ከሌለሽ ሰዉም በእናትሽ መፍረዱን ትቶ ባንቺ ይፈርዳል። ለዚያ እሷን ላለማስከፋት ሞክሪ። ቢያስከፋሽም ያዘዘችሽን አድርጊ። የማዳላቱ ነገር በተለይ ለቤቱ ታላቅ ለሆነ ሰው የተለመደ ነው። በቤቴ የመጀመሪያ ልጅ ነኝ። ቤት ውስጥ ለኔና ለመጨረሻው ወንድሜ የማይሰጥ ብር እና እንክብካቤ ለሁለተኛው ወንድሜ ይንበሸበሻል።😁 ታድያ እኔ ደስተኛ ነኝ። ምንም የሚያስከፋ ነገር የለውም። እኔ የተሻለ የማሰብና የመስራት አቅም ስላለኝ ከቤት ውርስ እንኳ አልፈልግም። ለወንድሞቼ ነው የምተውላቸው። በሰይጣን ተባባሪነት ባንቺ ላይ መድሎ እየተፈፀመ ሊመስልሽ ይችላል። መድሎ ቢኖር እንኳ ለወንድምና እህቶችሽ ለተደረገ ነገር ደስተኛ ሁኚ። ይህን ማድረግሽ ጥቅሙ 1, እንድትበሳጪ የፈለገችውን እናትሽን ደስተኛ በመሆንሽ ታበሳጫታለሽ (አነጋገሬ ልክ ነው??🙄) 2, የቤታችሁን መረበሽ ለሚፈልግ ጠላት እና ሰይጣን በር ትዘጊያለሽ 3, የገዛ ወንድምና እህቶችሽን ጠላት ከማድረግ ትተርፊያለሽ። 3, ወንድምና እህቶችሽም አንቺ እየተገለልሽ መሆንሽን ተረድተው ትኩረት ያደርጉልሻል። ስለዚህ መታገስሽ ከሁሉ በፊት ይሁን።
Dec 01, 2022