በፍጡራንና ፈጣሪ መካከል ድርሻ የተሰጠው ሰውን ለማገልገል ተራዳኢው መልአክ ጠባቂ የእስራኤል የመላእክት አለቃ ስሙ ነው ሚካኤል አማላጅ ነው ሚካኤል(፪) የአምላክ ባለሟል ለነሙሴ ለህዝበ እስራኤል ፈርዖን እንደገና ልቡ ተጸጽቶ ሲከታተላቸው ጦሩን አስከትቶ ይመራቸው ጀመር ሚካኤል በፋና ሌሊቱን በብርሃን ቀኑን በደመና አዝማች ሙሴ እንደታዘዘው አነሳ በትሩን እጆቹን ዘረጋ ገሠፀው ባህሩን እንደ ግንብ ቆመ ባህረ ኤርትራ በደረቅ አለፉ እስራኤል በተራ አዝማች በአፎሚያ ላይ ሲፎክር ጠላት ፈጥነህ የደረስከው ሊቀ መላእክት እኛንም ጠብቀን ከክፉ መቅሰፍት ፈጥነህ ድረስልን ሁነን እረዳት አዝማች መልአኩ ሚካኤል አማላጃችን እንለምንሃለን እንድትጠብቀን አምላክ በፍርድ ቀን ጻድቃንን ሲጠራ ዋስ ጠባቂ ሁነን ሚካኤል አደራ
Nov 28, 2022