Selam endet nachu 2tiyake neberegn for Orthodox trident mastika tsom alew? 2 yekdase tsebel yekorebe sew bicha nw metetat yemichilw? yaskedese sw metetat ayichlm?
Nov 27, 2022ከ2 ልጀመር። የቅዳሴ ጸበል (ማየ መቁረር) ያስቀደሰ ሰው መጠጣት አይችልም። ማየ መቁረር መጠጣት የሚችለው የቆረበ ሰው ብቻ ነው። ምክንያቱም የማየ መቁረር አስፈላጊነት በጥርስ አልያም በድድ ለሚቀር የጌታ ቅዱስ ስጋ ማውረጃ አንድም አፍ ማደፊያ ሲሆን ይኽን ጸበል ከመሬት ማንጠፍም ሆነ በእጅ አፍስሶ ዓይን ላይ ማፍሰስ አይቻልም። ቅድስት ቤተክርሰቲያን ለማትቆርቡ ምዕመናን የምትሰጥበት ምክንያት ወደ ጌታ ስጋና ደም እንድትቀርቡ ተስፋ በመቁረጥ እንዳትርቁ በሚል እንጂ ማየ መቁረር ለቆራቢ ብቻ የተፈቀደ ነው። #1 ትሪደንት ጾም አለው የለውም ተብሎ አይጠየቅም። የሆነ ሆኖ ሰለስቱ ምዕት አንድ ነገር ጾም አለው የለውም በሚል ክርክር ቢነሳ ለጾም አድሉ ሲሉ ትዕዛዝን አዝዘዋል ስለሆነም ትሪደንት አለው የለውም ለሚለው ጥያቄ ለጾም በማድላት ትሪደንትን አለማኘክ የክርስቲያን ግብር ነው።
Nov 27, 2022