ሰላም ሰዎች ምን መሰላችሁ አዲት የወደድኳት ልጅ ነበረች ለረጅም ጊዜ ማለት ለ አንድ አመት ፍቅሬን ሳልነግራት አስካሁን ቆይቻለው ድፍረቱን አጣሁ ምን ባደርግ ይሻላል ነግሬአት ደሞ ባትቀበለኝስ በጣም ጨቆኛል ምን ላድርግ ሰዎች እባካችሁ መላ በሉኝ
Nov 26, 2022ማፍቀር ፀጋ ነው ግን በግዜው ሲሆን ያማረ ይሆናል ስለዚህ ገና ራስህን በሰው ጫንቃ( ቤተሰብ) ላይ ሆነህ ከሆነ እንዲህ አይነቱ ሀሳብ የተጠናወተህ ላሽ ላሽ በለው ቅድሚያ ራስህን ማፍቀር ይቀድማል:: ራስን ማፍቀር ማለት(ለራስ ግዜ መስጠት/ራስን ከጥገኝነት ማላቀቅ/ራስን በፋይናንሻሊም ሜንታሊ የላቀ(ብቁ) ማድረግ ማለት ነው:: ስለዚህ በላይኛው ዴፍኒሽን መሰረት ሬዲ ነኝ(ራሴን አፍቅሪያለሁ) ብለህ ከደመደምክ ደፈር ብለህ በሙሉ ኮንፊደንስ ጠይቅ.. ነገር ግን ከጥያቄህ እንደምገምተው ገና ዝግጁ አይደለህም ብትሆን ኖሮ እንዲህ አይነቱ ፍራቻ አይከሰትብህም ነበር ስለዚህ ፍራቻህ በምክንያት ነውና መለስ ብለህ ራስህን አዳምጠው አነጋግረው... 😇መልካም የመነቃቃት ዘመን ይሁንልህ ወንድም አለም
Nov 27, 2022