ህይወቴን በዝሙት ኃጢአት ጭምልቅልቅ አድርጌያታለሁ በዚህም የጥፋተኝነት ስሜት እየተሰማኝ ስለሆነ ንስሐ ለመግባት አስቤያለሁ አሁን ላይ ባለሁበት ቦታ ግን ንስሐ መግባት አልቻልኩም ቢያንስ ከ6 ወር በኃላ በርገጠኝነት ኃሳቤ ሙሉ ይሆናል እስከ እዛ ድረስ ግን ምንም ስራ መስራት አልቻልኩም ማለት ፈጣሪ ከኔ እንደራቀና ንስሐ ካልገባሁ በቀር የምሰራው ሁሉ አልሳካ የሚል እየመሰለኝ ነው...ደግሞም እየሆነ ነው ፀሎት አላደርግም coz ፈጣሪ የሚሰማኝ አይመስለኝም so በዚህ ላይ ምንድን ነው ሀሳባችሁ ሰው ከነ ኃጢአቱ ሆኖ ፈጣሪ አይረዳውም ብላችሁ ታስባላችሁ??? የት ነው ያለኸው ለምን አሁን ንስሐ አትገባም አትበሉኝ 🙏🙏🙏
Nov 24, 2022ወንድሜ እንዴት አለህ; እዚህ ጋር ያለዉት ለምን እንዲህ አደረክ ለምን እንዲህ ሆነ ለማለት አይደለም፡፡ ማንም ከሀጢያት የጸዳ የለም፡፡ ሁሉም ሀጥያትን ሰርቷል፡፡ ሁሉም፡፡ ይህንን የምለዉ አንተን ለማጽናናት አይደለም ፡፡ እዉነታዉ እሱ ስለሆነ ነዉ፡፡ ዝሙት ሰርታለች ተብላ በአደባባይ በድንጋይ ልትወገር ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ተጎትታ የመጣችዉን ሴት አስታወስካት; እሷ ሴት ሀጢያቷ በገሀድ በመታየቱ ጥፋተኛ ናት ሀጥያት ሰርታለች እና ትወገር ብለዉ ይዘዋት መጡ እሱ ግን ምን አለ ‹‹ ከእናንተ መሀል ሀጥያተኛ ያልሆነ ቢኖር ይዉገራት ›› ታዲያ ማንም እሷን ለመዉገር ጉልበት አልነበረዉም ፣ ሁሉም በድብቅ የሰራዉ ነገርግን ከአምላኩ ሊሸሽገዉ ያልቻለዉ ሀጥያት ስላለበት ነዉ ፡፡ አንተም ወንድሜ ዛሬ ላይ ይህን ማለትህ ፣ ሀጥያተኛ ነኝ አጥፍቻለዉ ማለትህ ከማንም ዝቅ አያደርግህም፣ ከማንም፡፡ እንደዉም ከሀጥያትህ ለመመለስ አንድ እርምጃ የተራመድክ ሰዉ ነህ፡፡ አምላካችን እግዚአብሄር ምን እንደሚጠላ ታዉቃለህ ; ሀጥያትን ይጠላታል ሀጢያተኛን ግን አይጠላም፡፡ አባት ልጁን ፈጽሞ ሊጠላ አይችልማ፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ አባታችን ነዉ ፡፡ ያንተ ፣ የኔ ፣ የሁላችን አባት ነዉ፡፡ አይደለም ፊቱን ለሚሹ እና ለሚፈልጉት ቀርቶ ለማይፈልጉት እና ፊታቸዉን ላሸሹበት እንኳን አባት ነዉ፡፡ ስለዚህ አልረፈደብህም፣ አባትህ አሁንም የአንተን መመለስ ይፈልጋል፣ ይጠብቃል፡፡ ‹‹የጴጥሮስን እንባ›› ስጠኝ በለዉ ፡፡ በእንባ ፣ በለቅሶ ወደ አንተ ልመለስ በለዉ ፡፡ መቼም በሩን አይዘጋብህም ፣ እመነኝ መቼም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር አይወደኝም ብለህ በፍጹም አታስብ፣ ሀጥያት ስለሰራዉ ጸሎቴን አይሰማኝም አትበል፡፡ አንድ ልጁን ወደ አለም ሲልክ እኮ 99ኙን በጎች ትቶ አንድ የጠፋበትን ፍለጋ ነዉ የላከዉ ፡፡ ለአንተ ብሎ ከተሰቀለልህ እና ነፍሱን እንኳን ሳይሰስት ከሰጠህ ታዲያ አንተ ይህን ስላደረክ ሚጠላህ እና አልፈልገዉም የሚልህ ይመስልሀል; ለሰቀሉት እና ለገደሉት እንኳን ምህረትን የለመነ አባት እኮ ነዉ፡፡ ስለዚህ ወንድሜ እመነኝ ማርያምን በፍጹም አይጠላህም፡፡ ስለዚህ በእንባ እንዲህ አደረኩኝ አንተንም አሳዘንኩህ ብለህ ይቅርታን ጠይቀዉ ፡፡ ከልብህ አልቅስ ይቅር ይልሀል እሺ ወንድሜ፡፡ በፍጹም እንደሰዉ አይደለም ይቅር ብሎ ሀጢያትህን እንኳን የማይቆጥር ፈጽሞ የሚረሳ አባት ነዉና ይቅር በለኝ በለዉ፡፡ እኔም ጸልይልሀለዉ እሺ፡፡
Nov 25, 2022