Hey guys zare mn lelachu meselachu ezi bot lay bezu gize sle "v" yweral like v must nw mnamn stuff ena ene endemasbew kehone the first thing is ur ❤️ heart n luv right so Ena wendochm hone girls v mnamn atebelu cuz ene bezuraye even be teklili tegabtew mefatat yederesu alu hulum aydelm gn gn endemesfert meyaz alebet beye alasbm Ena hasab endsetubet felge nbr guys beteley demo dero v girl nw mefelgew nw belachu hasabachehun yaskeyerech miset or gf plss tell ussss tnx en advance
Nov 23, 2022መታወቅ ያለበት አስቀድሞ ጋብቻ የሚፈቀደው በሥርዐተ ተክሊል ብቻ እንደሆነ ሲሆን። ከሰው ስህተት አይጠፋምና ከጋብቻ በፊት በተከሰተ ሩካቤ ምክንያት ድንግልና ባይኖር ጋብቻ በሥርዐተ ቁርባን የሚፈፀም ይሆናል። ከነዚኽ ከ2ቱ ሥርዐት የወጣን ጋብቻ ቤተክርቲያን ጋብቻ ብላ አታጸድቀውም በእግዚአብሔር ፊትም ባልና ሚስት አያስብልም። (ከዚ ውጪ ጋብቻ የፈጸማችኹ ቁረቡ በጋራ) " በተክሊል ተጋብተው እስከ መፋታት የደረሱ አሉ ላልሽው ልክ ነሽ ይኖራሉ። የተፋቱበትን ምክንያት እግዚአብሔርና ባለቤቶቹ ናቸው የሚያውቁት። የቀደመ ድንግልናቸው ግን በራሱ ላለመፋታት ዋስትና አይሆንም። በትዳር ላይ ድንግልና ወሳኝ የሆነበት የራሱ ሁነቶች ግን አሉ። #አስቀድሞ ድንግል ነው የምፈልገው ብላችኹ ሀሳብ ያስቀየረች ሚስት ወይም ፍቅረኛ አለች ወይ ላልሽው። ትኖራለች። ይኽንም በ2 ከፍለሽ መመልከት ትችያለሽ። አንዱ ከዘማዊት ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባል እንደተባለ በተንኮሏ አስታ (ቆብ እስከማስጣል) በወጥመዶ ጠልፋ የምትጥልና ሀሳብ የምታስቀይር መንገድ የምታስለውጥ ስትሆን ሌላኛዋ ከዛ በተቃራኒ በቀደመ ስራዋ አፍራ ወደ እግዚአብሔር ተመልሳ በጥበብና በሞገስ ከፍ ብላ መስቀሉን በጋራ ለመሸከም ትከሻዋን አደንድና የተገኘች ናት። እነዚ ሁለቱ ሀሳብ ያስቀይራሉ። እና ድንግልናችሁን ጠብቁ። የልደት ስጦታ ይመስል በልደት ቀን ለመስጠት ተኳኩላችኹ አትውጡ። ወንድዬውም እያደመጥክ። ድንግልና እንኳን ለባል አልያ ለሚስት አይደለም ለእግዚአብሔር እንኳ የሚሰጥ ውድ ስጦታ ነው። እንጠባበቅ ወገን። እኛ ስንፈልግ እናንተ ከልክሉን። እናንተ ስትፈልጉ እኛም እንከልክላችኹ። ስሜት እንግዳ ነውና ሲመጣ ባለማስተናገድ እንሸኘው በዚ መንገድ።
Nov 24, 2022