ሰላም ቤተሰብ ማዳመጥ የሚችል ጆሮ እያላቹ በትክክል እንዳማትሰሙ፤ ማየት የሚችል ዓይን እያላቹ በትክክል እንደማታዩ(አይምሮአቹ እነዚህን ነገሮች መተርጎም አይችልም ብላቹ ብትፈሩ አይምሮአቹ አምኖ ቢቀበል እና ከሚሰሙና ከሚታዩ ነገሮች ልራቅና አይምሮዬን እንዳይጨነቅ ብትሉም እነዚህ ነገሮች የሌሉበት ቦታ የለም።እስቲ እነደዚያ ያለ ሌላ የፋልስፋና አለም ውስጥ ገብቶ መውጣት ላቃተው ሰው እስቲ ከዚህ ስሜት የመውጫ ምክር ስጡ ብትባሉ ምን ትመክሩታላቹ?ማለቴ ሳይኮሎጂ አናግር ከሚለው ውጪ።
Nov 14, 2022ማለት አንድ ሰው ውሻ ብሎ ሲሰድብህ አንተ ደሞ በስምህ የጠራህ መስሎህ አቤት እንደምትለው አይነት ማለት ነው?....ሰዎች የሚሉት ላንተ እነሱ የተናገሩት ራሱ አይደርሰኝም ሌላ ነገር ነው እኔጋ የሚደርሰው ብለህ የምታስብ ከሆነ እኛም የምንሰጥህ ምክር በሌላ መልኩ ተገልብጦ አለመድረሱን በምን እርግጠኛ ትሆናለህ? እንደዚ አይነት ነገር ከአይምሮህ ጋር ስትላፋ የምትፈጥረው ቅዥብርብር አለም ነው።ከአንድ ሰው ጋር በንግግር ተግባብተህ የምትፈልገውን ነገር አገኘህ ማለት ጆሮህ በትክክል አዳምጧል አፍህም ያሰብከውን አውርቷል ማለት ነው።የአይንህ ጉዳይ ደሞ ግርግዳ ፊት ለፊትህ እያየህ ዝም ብለህ ሂድ እስኪ አናትህ የፈለጠህ ነገር እንዳለ ከተሰማህ አይንህ እና አዕምሮህ ተግባብተው መረጃውን ሳትጋጭ በፊት እንዳቀበሉህ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ። practical የሆነ መመሪያ ነው የሰጠውህ😁
Nov 16, 2022