ሰላም እኔ ምላችሁ አከባቢያችሁ ላይ ያለ በትምህርት በግብርና በሠላም በሥርዓተ ጾታ እኩልነት ወዘተ ከእነዚህ ነገሮች አንፃር እንዲሻሻሉ የምትፈልጓቸው መፍትሔ የሚሹ ነገሮች ካሉ አካፍሉን እስቲ?
Nov 12, 2022ትምህርታዊዉ ላይ ብሬ አውቆበታል ባይ ነኝ በግብርናው ላይ ግን ገና ብዙ ይቀረናል ከምር መንግስት ለከተማ ልማት እየሰራ እንዳለው ግብርናው ላይም focus ማረግ አለበት ህዝቡ እየተራበ ከተማ ቢያምር ምን ዋጋ አለው በሰላም ማስከበር ላይ ያለኝ ሃሳብ 1 ነው እሱም = ህግ አስከባሪዎች በድንብ ልብሳቸው ሳይሆን በጭንቅላታቸው ማሰብ እስካልጀመሩ ድረስ ለውጥ አልጠብቅም እኔ በበኩሌ የጾታ እኩልነት ላይ ያለኝ ሃሳብ ጥቂት ነው ይሄን ጉዳይ ለመቅረፍ ቤተሰብ ላይ ነው ቅድሚያ መስራት ያለበት ከትንሽ ተጀምሮ ነው ወደ ከፍታው የሚወጣው እዚህ ላይ 1 የምጨምረው ነገር ቢኖር ሃይማኖታዊ ጉዳይ ነው መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ እንደሆኑ ነው ህገመንግስት የሚደነግገው ስለዚህ ሁለቱም ድንበራቸውን ይያዙ ባይ ነኝ ፖለቲከኞችም አርፈው ፖለቲካቸውን ይስበኩ የማያውቁትን የእምነት አስተምህሮ እየተፈላሰፉ ደህና ተከባብሮ ይኖር የነበረውን ህዝብ አያባሉት አንዳንድ መንፈሳዊ ነን ባዮችም ይከበሩ እና ይቀመጡ ድሮ የሌለ ያልነበር ስረአት እያመጡ ህዝቡ ላይ አየለድፉ በእምነት ስም የሚነግዱትንም በህግ ይቅጡልን
Nov 13, 2022