ሰላም እዴት ናቹሁ ምን መሸላቹሁ እኔ አይናፋር ነኝ ማለት በቃ ከሰው ጋር መግባባት አልችል በዛለይ ዝምተኛ ነኝ ሌላው ደሞ የሚያስጨንቀኝ ነገር እኔ በመገድ ሳልፍ እሚያየኝ ሰው ሁሉ ስለኔ የሚያወራ ይመስለኝና እሸማቀቃለሁ በቃ እኔጃ እራሴን እስከመጥላት ደርሻለሁ ህይወት እያስጠላኝ ነው ፡፡ እባካቹሁ በፈጣሪ ስም ይዧቹሃለሁ እዲህ አይነት ነገር መሮኛል ምን ማረግ እዳለብኝ ብትነግሩኝ ፡፡ ለትብብራቹሁ አመሰግናለሁ
Nov 12, 2022አይናፋርነቱ እና ዝምተኝነቱ በሂደት የሚቀረፍ ሲሆን ሰዎች ስለኔ የሚያወሩ ይመስለኛል ያለከው ግን ከባድ ነገር ስለሆነ ለራስ ያለህ አመለካከት ከፍ ማለት አለበት። በዚህ ምድር ላይ አንተ ልዩና ፈጣሪ በክብር እንደፈጠረህ ማሰብ አለብህ።
Nov 13, 2022