Hey guys eski zare 1serious yehone bzu sew lay happen eyarege yale even ezih yegroup tyake lay enquan at least one question in a day ayalew siteyek. Ena am so confused ewunet suicide kenegeroch mamlecha kalubn chigroch medebekiya ena mewucha menged yihonal blachu tasbalachu Mns kebad chigr wust bngeba yefeteren amlak lesu mewucha menged bnteyikew yemikelekil amlak hono nw Weyis erasn matfat ...idk mn malet endalebgh bzu sew yihen menged simert siyadergewum eyayew nw enam gra gebtoghal WHAT'S HAPPENING??? Eski enante mn tasbalachu Yemisemachun hasab share btadergugh at least one person madan enchilalen biyans exih lay yalu yihen yasebu lijoch limelesubet yichilalu .. TXU 👍👍👍
Nov 08, 2022እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ራስን ማጥፍት ያደጉት ሀገራት ችግር ነበር።አሁን ላይ ደሞ ፊቱን ወደኛም ማዞር ጀምራል። እግዚአብሔር ይመስገን እስካሁን አንድም ገበሬ እራሱን አጠፍ የሚል ወሬ አልሰማሁም።ግን ለምን?...ለምን በገጠራማው በጣም አስቸጋሪ በሚባሉ ቦታዎች ያሉ ሰዎች እራሳቸውን አያጠፉም?....ብዙ km አቋርጠው በጀርባቸው ውሀ አዝለው መምጣት ሳያንገሸግሻቸው ቀርቶ?... እንደነ እይታ ከሆነ ራሳቸውን የሚያጠፉት ሰዎች በብዛትም ከሚገኙባቸው ቦታዎች አንፃር ምክንያቱ የተለያየም ቢሆን እንኳ አንድ የሚያረጓቸው ጥቂት ጉዳዮች አሉ። 1)ከእምነት ተቋማት መራቅ ምን ለማለት ነው ቢያንስ በእምነቱ ጠንካራ የሆነ ሰው ራሱን ማጥፍቱ በራሱ ሀጥያት እንደሆነና የገጠመውንም ችግር ከአምላኩ ጋር መወጣት እንደሚችል ያምናል። 2)ያለ አግባብ social ሚዲያ ላይ መዋል ይሄ እንደውም ዋንኛ ችገሩ ይመስለኛል ምክንያቱም አብዛኞቹ s.m ተጠቃሚዎች በማህበራዊ ህይወታቸው ላይ ደካማ ናቸው።ከቤተሰባቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት የላቸውም።አንድ ነገር ቢያጋጥማቸው ችግራቸውን የሚያማክሩት የልብ ጓደኛ የላቸውም ምንም እንኳ ችግርሽን ባይቀርፍልሽም ችግርሽን ለጋደኛሽ ስነግሪኮ የሆነ ቅልል ይልሻል።እና ያንን ችግር የሚረዳሽ ቀርቶ የሚሰማሽ ሰው ስታጪ አስቢው እንግዲ🙄 3)ያለ ስራ መዋል ስራ ሲፈታ እና ትንሽ ችግር ሲያጋጥምሽ አዕምሮሽ ብዙ ነገር ያሳስብሻል በስተመጨረሻ እራስሽን ማጥፍት ታስቢያለሽ ደጋግመሽ ባሰብሽ ቁጥር ደሞ በህይወትሽ ላይ መገለጥ ይጀምራል።...በነገረችን ላይ ቅድም ያልኳቸው በጣም በችግር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችም እራሳቸውን እንዳያጠፉ ያረጋቸው ቀኑን ሙሉ በስራ መወጠራቸው እና ከሰዎች ጋር ያላቸውም ተግባቦት ይመስለኛል።ያው ሴቶቹን ቡናው ያገናኛቸዋል ወንዶቹም መሸታ ቤት።ቀኑን ደሞ በስራ ሲዳክሩ ስለሚውሉ እንኳን እራስን ማጥፍት ምግብ መች ልብላ ምን ልልበስ የሚል ሀሳብ እንኳ አይመጣባቸውም።ከእምነት ተቋማት ጋርም ያላቸውን ግንኙነት ማንሳት ይቻላል። ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል ግን አሁን ካልኳቸውን ችግሮች እራሱ ብዙ ለውጥ ማምጣት ይቻላልና ይብቃኝ።...ይህ ግን የኔ እይታ ና ምክር ብቻ ነው👀😊 ጉዳዩ አሳስቦሽ የጠየቅሽውን ልጅ ግን ሳላመሰግን ባልፍ ሀጥያት ይሆንብኛልና እጅግ በጣም እናመሰግናለን🙏🙏🙏
Nov 09, 2022