ፈጣሪን ለምንድነው የምንፈራው? መልካም ስለሆነ ነው? ወይስ መጥፎ ስለሆነ? ፈጣሪስ መፈራት የፈለገው ለምንድነው?
Nov 07, 2022ፈጣሪን ፍራ ሲባል እሱ ፊት ስሙ ሲጠራ ተንቀጥቀጥ፣ ቃሉን ስትሰማ ሽሽ ማለት አይደለም። በርግጥ አምላክ ራሱን በመለኮቱ ቢገለጥ እንደ ሰም መቅለጣችን ባይቀርም እንደዛ ያለውን ፍራቻ አይደለም የተባለው። ልጅ የሚወደውን አባቱን እንደሚፈራ፣ ሚስትም ውዱ ባሏን፣ ባልም ውዷ ሚስቱን እንደሚፈራ ሁሉ አንተም እግዚአብሔርን ፍራ ለማለት ነው። ሚስት ባሏን ፈርታ እሱ የነገራት ከማድረግ ብትቆጠብ ቡጢውን ሳይሆን ፍቅሩን ከሆነ ባልም ሚስቱን የሚፈራው ቁጣዋን ሳይሆን ፍቅሯን ፈርቶ ማድረግ ከሌለበት ነገር ከተቆጠበ መልካም እንደሚሆን ሁሉ እግዚአብሔርም የሚፈራው ከፍቅር የተነሳ እንጂ ይቀስፈኛል/ሲኦል ይወረውረኛል በሚል አኳኋን መሆን የለበትም። ቀደምት አበው እንኳን ሲገልጹት ‟የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ሲሆን መጨረሻው ደሞ እግዚአብሔርን መውደድ ነው።” ብለው ያስቀምጡታል
Nov 08, 2022