Sile Mahsa Amani semtachuhaal biyye assiballehu. What are your thoughts on the whole situation? Min tassiballachu sile motua and iyyetemenawene silaallewu tekaawumo? Especially my Islam people, what do you think?
Nov 05, 2022ነገሩ ላይመለከትህ ይችላል። ግን ትንሽ ነገር ልበልህ። በመጀመሪያ ኢራን ውስጥ ከ95% በላይ ያለው ህዝብ እኛ የምናውቀውን ኢስላም የሚከተሉ አይደሉም። ጥቅል ስማቸውም "ሺዓ" ነው። የተቀረው አለም ውስጥ ያሉ የኢስላም ሊቃውንት እነዚህን ህዝቦች በአላህ የካዱ/ካፊሮች አድርገው ነው የበየኑት። እነዚህ ሺዓዎች ሌላው አለም ላይ ያለውን ሙስሊም በአላህ የካደ/ካፊር ነው ብለው ነው የሚያስቡት። ስለዚህ በመሃላችን ትልቅ ልዩነት አለ። ክርስቲያኖችን በምናይበት አይን ነው ሺዓዎችን የምናየው። ይህን ካልኩህ ወዲያ.. አላህ ሴቶችን ሂጃብ እንዲለብሱ አዟል። ይህም ለራሳቸው ደህንነት ሲባል ነው። ከላይ ጸጉሯ እስከ ታች እግሯ የተሸፈነች ሴት እና ተገላልጣ የለበሰች ሴት ብትኖር በባለጌ ወንድ ለመለከፍ የቀረበችው የትኛዋ እንደሆነች የታወቀ ነው። አንድ ሰው ማመንም መካድም አላህ መብቱን ሰጥቶታል። ነገር ግን ውጤቱንም አብሮ መቀበሉ ግድ ነው። ይህን ስል አንድ ሰው ሙስሊም ከሆነ ኢስላም ለሰጠው ትዕዛዝ ታዛዥ መሆን አለበት። መስገድ፣ መፆም፣ አይንን ከተቃራኒ ፆታ ማቀብ፣ ሂጃብን መልበስ፣ ነፍስን አለማጥፋት (with exceptions)፣ አለመዋሸት እና የመሳሰሉትን መተግበተር አለበት። ይህ ሙስሊም በመሆኑ የሚጠብቀው ግዴታ ሲሆን ውጤቱም ዘለዓለማዊ ደስታን መጎናጸፍ ነው። ሙስሊም ባለመሆኑ ሙስሊም ሆኖ የሚያገኘውን ምንዳ ማጣቱ ውጤቱ ነው፤ ዘለዓለማዊ ደስታን ማጣት! ስለማህሳ አሚኒ (ሺዓ ሙስሊም ትሁን የሌላ እምነት ተከታይ እውቀቱ የለኝም) ሺዓዎቹ ምን እንደሚያስቡ ባላውቅም በግሌ መጀመሪያ ችግሩ ከቤተሰቦቿ ነው። ቤተሰቦቿ እርሷን ያሳደጉበት መንገድ ዛሬ ትልቅ ሆና ተንጸባርቋል። ኢስላም ሂጃብን መልበስ ግዴታ ካደረገ መልበስ አለባት።(ሙስሊም ነኝ ብላ እስካሰበች ድረስ) የአገሪቱ ህግ ሂጃብን መልበስ ግዴታ ካደረገ መተግበር ነበረባት። ይህን ባታደርግ ምድራዊም ይሁን ሰማያዊ ቅጣት ይጠብቃታል። ስለ ሰማያዊ ቅጣቱ አላህ ይወቀው። ምድራዊ ቅጣቷ ላይ ግን እንዴት ነው የሚለው ነው አሁን ያለውን ነገር የፈጠረው። "በፖሊስ ክፉኛ ተመትታ ሆስፒታል ገብታ ሞተች" እንዲህ ነበር ያነበብኩት። እንደ ኢስላም ሸሪዓ አንድ ሰው ወንጀል ቢሰራ ማንም ተነስቶ የዛን ወንጀል ቅጣት አይሰጥም። ለምሳሌ አንድ ያላገባ ወጣት ዝሙት ቢፈጽም ዝሙት ስለፈጸመ ብቻ ማንም ተነስቶ የተበየነበትን 80 ጅራፍ አይገርፈውም። የወንጀሉን ድርጊት አይተው ቅጣቱን የሚበይኑ ሊቃውንት አሉ። በነርሱ ትዕዛዝ ለዚህ ወንጀል የተመደበ ቅጣት ፈጻሚ 80 ይገርፈዋል። ከዚያም ከወንጀሉ ይነጻል። በተመሳሳዩ 'ማህሳ ኣሚኒ' ሂጃቡን አልለብስም ስትል አንድ ተራ ፖሊስ ተነስቶ ለሞት የሚያበቃ ምት መምታቱ በምንም መልኩ ትክክል አይደለም። ኢስላማዊና ፖለቲካዊ ህግ አለ። እርሷን ወስዶ ለህግ ነው ማስረከብ የነበረበት። እንደ አመዛዛኝ ሰው ብናየውም ሴት ላይ እጅ ማንሳት ወንድነት/ህግ አስከባሪነት አይደለም። የሆነው ሆኖ እርሷም ሞተች። ትክክለኛ ሙስሊም ከነበረች አላህ ወንጀሎቿን ይማርላት። የኛንም ወንጀል ይማር። ሙስሊም ካልነበረች ለቤተሰቦቿና ወዳጆቿ መጽናናቱን ተመኘሁ። ከሷ ሞት በኋላ ተከትለው የመጡ ነገሮች ሂጃብን ማውለቅ፣ ማቃጠል፣ ጸጉርን መቁረጥ፣ የሀይማኖት መሪዎቻቸውን መምታት፣ መስደብ፣ አገር ገዢን ማመጽ በፍጹም ትክክል አይደለም። ለርሷ ድጋፋቸውን ለመግለፅ ሂጃባቸውን አውልቀው ያቃጠሉ ሴቶች መጀመሪያም በልባቸው ውስጥ የነበረውን ነው ያወጡት። ሂጃብን እንደ እስር ቤት የቆጠሩ ነበሩ። በነርሱ እይታ ነጻ ወጥተዋል። መንግስታቸውንና የሀይማኖት መሪዎቻቸውን ያመጹትም መጀመሪያ በገዢው ፓርቲ ድብቅ ፖለቲካዊ ተቃውሞ ነበራቸው። እርሱን ነው ያሳዩት። (አገሪቱ በሀይማኖት መሪዎች ነው የምትመራው) ለጥያቄህ መልስ አጊኝተሃል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
Nov 06, 2022