በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ለ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እራስን መውደድ በኛ ሀይማኖት እንዴት ይታያል ? አንድ ተራ ኑሮ(መንፈሳዊያልሆነ) እሚኖር ሰዉ እራሱን መውደድ አሚችለው እንዴት ነው ? / ይችላል ? በሰራው ሀጥያት እራሱን የሚፀየፍ ሰው እንዴት እራሱን ይቅር ማለት ይችላል ? እንዴትስ እግዚአብሔር still እንደሚወድ ማመን ይችላል ? የሚሰራው ሀጥያት የ ሚገል ግን no one notice ማረግ የ ማይችለው ሀጥያት ነው እና እንዴት ማቆም ይችላል ? ሀጥያቱ እንዳይገለኝ ብሎ ፈርቶ ሳይሆን ፈጣሪውን ላለማሳዘን ሲል
Nov 04, 20221) እራስን መውደድ በሁለት አተረጓጎም እናያለን። -ራስ ወዳድነት (Selfishness) ከሆነ ትክክል እይመጣም - ለራስ ተገቢውን ቦታ መስጠት ከሆነ ግን እሱ በአብዛኛው አስፈላጊ ነው። በመንፈሳዊው ጎን ክርስቶስ ኢየሱስ መስቀል ላይ ያረፈለት፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የሰጠው፣ በምሕረቱ ብዛት የሚኖር መሆኑን መቀበል አለበት። በዓለማዊውም ክቡር ሰው መሆኑን፣ እንደ አቅሙ እራሱን ቤተሰቡን ማገዝ የሚችል መሆኑን ማወቅ አለበት። እነኚ ነገሮችን ሲያደርግ ግን selfishness ወይም ሌላውን ጎድቶ እሱን ብቻ የሚጠቅም መንገድ ብቻ መጓዝም የለበትም። ቢሆንም ግን ዓለም ላይ ያለው ሰው ፍጹም ገዳማዊ ባለመሆኑ Selfish በመሆን ፍራቻም እራሱን እና ቤተሰቡን ወደ ጉዳት የሚመሩ ነገሮችን ባያደርግ መልካም ነው። 2) ማንም ልቡናው ያልተሰወረበት ሰው የራሱን ኃጢአት መጸየፉ አይቀርም። ሰው እግዚአብሔር ልቡናውን በከፈተለት ልክ ኃጢአቱን ይበልጥ እየተጸየፈ ይመጣል። ከገዳማዊያን አበው አንድ ታሪክ ራሱ አለ 'አንድ ቀን አዲስ አርድእት የሆነ መነኩሴ በህልም ራእይ አየው ብሎ ለአበምኔቱ ይነግራል። እሳቸውም ‟ምን አየህ?” አሉት። "የሰማይ መላእክት እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ አየው" አላቸው። እሳቸውም "አይ ይሄ ተራ ህልም እንጂ ራእይ አይደለም። ጸልይ" አሉት። ሌላ ቀንም መጣ። "አባ ዛሬ ያየሁት ህልም ግን ራእይ ነው" አላቸው። እሳቸውም ምን እንደሆነ ጠየቁት። ‟የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆኝ ወሰደኝ። ሲኦልና ገነትን እዛ ውስጥ ያለውን ሁሉ አሳየኝ" አላቸው። "አይ ልጄ ይሄም አሁንም ተራ ህልም ነው። ተግተህ ጸልይ" ብለው አሁንም መለሱት። አሁንም ሌላ ቀን ተመለሰና "አባቴ ዛሬ ያየሁት ራእይ ግን እውነተኛ ነው። የእግዚአብሔር መልአክ ወደኔ መጣ፥ ትልቅ መጽሐፍ አውጥቶ ከልጅነቴ እስከነ እውቀቴ የሰራሁትን ኃጢአት ሁሉ ገለጠለኝ። እኔም እግዚአብሔርን እንዴት እንዳሳዘንኩ አይቼ ተጸጸትኩኝ" አላቸው። እሳቸውም "አሁን ገና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ራእይን ገለጠልህ" አሉት።'፨ በአጠቃልይ፣ ኃጢአት የሚገድል ቢሆንም ሁሉም ሰው እድፍ አለው። ከኃጢአት እድፍ የምንነጻው ትንሽ ትልቁን ኃጢአት chase እያረግን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ምሕረት በማሰብ ነው። ኃጢአትን አሯርጦ ማሳደድ አይቻልም፥ ጴጥሮስን የማይጠቅመውን ኃጢአትን ብቻ ሳይሆን የሚጠቅመውን የአሳ መረብ ያስጣለው የክርስቶስ ፍቅር ነው። ስለዚህ ከሁሉም መጀመርያ ፍቅረ እግዚአብሔር ይበልጣል። ኃጢአት ቢኖረን እንኳ ፍቅሩ ካለ ምሕረት ይገኛል።
Nov 05, 2022