ሰላም ቤተሰብ እንዴት ናችሁ በመጀመርያ ግን ምንም አይነት የዘር እና የጥላቻ ንግግር እንዲሁም ስድብ አልፈልግም አለመመለስ መብት ስለሆነ የትላንቱን የብልፅግና እና የህወሓት ስምምነት እንዴት አያችሁት ? እንደሚባለው ሰላም የሚያመጣ ከሆነ ጥሩ ነው ደስ ብሎኛል ምክንያቱም የሞተው እና እየሞተ ያለው ወጣት እያለቀሱ ያሉ የእናቶችና የህፃናት ድምፅ ብቻ ሁሉም ያማል.. ግን የሆነ ያልተዋጠልኝም ያልገባኝም ነገር አለ እሱም ህወሃት ከዚ ጦርነት ማግኘት የፈለገችው ምን ነበር አሁንስ ምን አግኝታ ነው ልትስማማ የቻለችው ነው ወይስ ወልቃይት እና ራያን ወደ ትግራይ ሊጠቀልልላት አስቦ ነው ይሄ ሰውየ ያለምንም ጥቅም ሁለት አመት ሙሉ አልተፋጁም መቼስ ምን ታስባላችሁ እናንተ
Nov 03, 2022ሁለቱም ያለምንም ጥቅም ተፋጁ! ህዝቡንም ፈጁት! በዚ ጦርነት የተሳካለት ሞትና ስቃይ ብቻ ነው
Nov 04, 2022