#Orthodox ሠላም እንዴት ናችሁ ጥያቄዬ አራቱ ወንጌላውያን ወንጌሉን መቼ ፃፉልን?
Nov 03, 20221. የማቴዎስ፡ወንጌል ፀሐፊው፦ማቴዎስ(የቀድሞ ስሙ ሌዊ ይባላል) የሚመሰለው፦በሰብዓ የተፃፈው፦ጌታ ከአረገ ፰ኛው ተፈፅሞ ፱ኛው ዓመት ሲጀመር(ቀላውዴዎስ ቄሳር በነገሰ በመጀመሪያው ዓመት) የተፃፈበት ቋንቋ፦በዕብራይስጥ 2. የማርቆስ፡ወንጌል ፀሐፊው፦ማርቆስ(የቀድሞ ስሙ ዮሐንስ ይባላል) የሚመሰለው፦በአንበሳ የተፃፈው፦ጌታ ከአረገ ፲፩ኛው ተፈፅሞ ፲፪ኛው ዓመት ሲጀመር(ቀላውዴዎስ ቄሳር በነገሰ በ፬ኛው ዓመት) የተፃፈበት ቋንቋ፦በሮማይስጥ 3. የሉቃስ፡ወንጌል ፀሐፊው፦ሉቃስ የሚመሰለው፦በላም የተፃፈው፦ጌታ ከአረገ ፳፩ኛው ተፈፅሞ ፳፪ኛው ዓመት ሲጀመር(ቀላውዴዎስ ቄሳር በነገሰ በ፲፬ኛው ዓመት) የተፃፈበት ቋንቋ፦በዮናኒ 4. የዮሐንስ፡ወንጌል ፀሐፊው፦ዮሐንስ የሚመሰለው፦በንስር የተፃፈው፦ጌታ ከአረገ ፴ኛው(፴፭ኛው)ዓመት(ኔሮን ቄሳር በነገሰ በ፰ኛው ዓመት) የተፃፈበት ቋንቋ፦በዮናኒ(ጽርዕ)
Nov 03, 2022