እኔ የኮሌጅ ተማሪ ነኝ ት/ት የጀመርኩት 2013 ሚያዚያ ላይ ነው፡፡ አሁን 2015 ት/ት ስንጀምር ሁለተኛ አመት ሁለተኛ ሴሚስተር ነው የጀመርኩት፡፡ ግን ሌላ ኮሌጅ የሚማሩት ጎደኞቸ አሁን ሶስተኛ አመት አንደኛ ሴሚስተር ነው፡፡እኔ ከሌሎቹ አንፃር አንድ ሴሚሰተር ወደሗላ ቀርቻለሁ፡፡ ትምህርት ስንጀምር ለት/ቤቱ ከሌሎች ኮሌጆች አንድ ሴሚስተር ወደሗላ ቀርተናል ይስተካከልልን ወደሗላ የቀረንበት ምክንያት ምንድን ነው ብለን አቤቱታ አቅርበን ነበር፡፡ በአሁኑ አመት ሶስት ሴሚስተር እንማርና የቀረብንን ይካካስልን ብለን ነበረ፡፡ ግን የኮሌጁ ድን ምንም ሊሰማንና ሊያሰተካክልልን አልፈለገም፡፡ የሰጠን ምላሽ ግደታ ለመመረቅ 4 አመት(48ወር) መማር አለባችሁ በ3 አመት ተኩል አትመረቁም(ከ2013 ሚያዚያ እስከ 2016 መጨረሻ) አራት አመት ስላልሞላ ማለቱ ነው፡፡ አሁን ጥያቄየ በት/ት ሚኒስተር ህግ መሠረት ግደታ እስከ 2017 አጋማሽ ድረሥ መማር አለብን ወይስ እኛ ያቀረብነው ጥያቄ ከህግ አንፃር ተገቢ ነው?
Nov 02, 2022Yegnam endeza new bakh
Nov 02, 2022