ሳላቀው ለውጭ ዜጋ ጋር በቴሌግራም እያወራሁ ነበር እና መታወቂያ እና ፎቶ ላክ ብለውኝ ልኬ ነበር ግን ሰዎቹ scammer ናቸው መሰለኝ አሁን ላይ text እየመለሱም አደለም ምን አይነት ችግር ሊያመጣብኝ ይችላል?አመሰግናለሁ
Oct 31, 2022ሰሞኑን የተስፋፋው አዲስ የማጭበርበርያ ዘዴ! ከሁለት ዓመት በፊት post የተደረገ ቢሆንም ሰሞኑን መሰል ማጭበርበሮች እየተበራከቱ በመጣታቸው በድጋሚ post የተደረገ ይህንን ጉዳይ ቢያንስ ከአምስት ሰዎች ስለሰማሁት ላጋራችሁ ወደድኩ። ጉዳዩ እንዲህ ነው: በመጀመርያ የውጭ ዜጎች (በአብዛኛው ነጮች) ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ሰዎች የፌስቡክ (የቴሌግራም) መልእክት ይልካሉ። በመልእክታቸው ውስጥም ኢትዮጵያ ለጉብኝት አልያም ለኢንቨስትመንት ሊመጡ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ። ይህንን ለማሳመንም በቪድዮ እየታዩ ያወራሉ። ከዛ ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ፣ ልብሶች፣ ስጦታዎች እና የመሳሰሉትን በሰው በኩል ልኬያለሁ ይላሉ። በዚህ መሀል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ወይም ያለች አንድ የድርጊቱ ተባባሪ "ከውጪ ገንዘብ እና እቃ መጥቶልሻል/መጥቶልሀል። ይህንን ለመውሰድ 30,000 ብር ይዘህ/ይዘሽ ነይ" ይባላል። ገንዘቡን የከፈለ ተበላ ማለት ነው። ከእንዲህ አይነት አጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ፣ መልእክቱን ለሌሎችም ያጋሩ!
Oct 31, 2022