ጥያቄዬ ለሙስሊሞች ነው ተዋረድኩላቹ ጠላታቹ ይዋረድ ፤ የሆነ መውሊድ ሞቅ ተደርጎ የሚከበርበት መስጊድ ያለበት ሰፈር እንግድነት ሄጄ ነበር ሰሞኑን 15 ቀን አልፎኛል እና ኡስታዙ ሲያስተምሩ በመሀል ጥያቄ ብዬ እጄን አውጥቼ ቆይ ድቤ ምናምን ግን ይፈቀዳል እንዴ እንዴት እያያቹ ዝም ትላላቹ አልኳቸው ለድቤ መፈቀድ 12 ሀዲስ አመጣልሀለው አሉኝ እኔ ደሞ ስንት ሰው እያየ ምዬ አታመጡም አልኳቸው ፤ 14 ሀዲስ ቁጠር ብለው ጀማው ፊት እያስቆጠሩ አነበቡልኝ እና ዞረብኝ ማመን ራሱ አቃተኝ ፤ እንቅልፍ እምቢ ብሎኝ ነው ያደርኩት በጠዋት ኡስታዜ ጋር ሄድኩና ኪታቡን ፎቶ አንስቼ ይዤ ነበር የሀዲሶቹን ምንጮችና ቁጥር እየነገርኩት አውጣልኝ አልኩት ፤ ፊቱ ደስ አላለኝም ግን ወጥሬ ያዝኩት ከቡኻሪ 2 ከሰሂህ ሙስሊም 1 በትክክል ያኛው ኡስታዝ እንዳሉት ተገኘ ሌሎቹ ኪታቦቹ የሉኝም አለኝ እና እንድትመልሱልኝ ምፈልገው እነ ኡስታዝ ሳዳት ከማል ከየት አምጥተው ነው ያሁሉ ነገር ሚያወሩት even እኮ ያመጣልኝ ሀዲስ ላይ መንዙማ እያሉ የሚጨፍሩትን ሚወዛወዙትን ሁላ ሰሀቦችም በነቢዩ ፊት ሰርተውታል ነው ሚለው እና ምንድነው ነገሩ ወንድሞቼ በቅንነት አስረዱኝ እባካችሁ
Oct 29, 2022ጥያቄው መደገሙ እንድጠረጥር አደረገኝ.. ምናልባት ከራሳቸው ወገን ሆነህ እነዚህን እያምታታህ ለማሳመን የፈበረክከው የውሸት ሀሳብ/ወሬ ቢሆንስ? የጠቀሱልህን ሰዲሥ አልፃፍከው.. እንዲሁ እየቀጠፍክ ቢሆንስ🤷🏽♂ ለማንኛውም ስለ መውሊዱም ስለ ዲቤ (መለስተኛ ዘፈን) ለማውራት ቦታው አይደለም ብለው መልስ ሰጥተውሃል። አረጋጋው!
Oct 30, 2022