ሰዎች እንዴት ናችሁ አሁን 19 አመቴ ነው እናም እስካሁን ምንም አይነት የፍቅር ግንኙነት ጀምሬ አላውቅም። በእርግጥ ከ elementary ጀምሮ ከወንዶች ጥያቄዎች ቢቀርቡልኝም አልተቀበልኩም።ያው አብዘሀኞቹ ግዜ ማሳለፊያ ቢሆኑም አንዳንዴ ቁምነገረኞችም አልጠፉም።ይህንን ስላችሁ ያን ያህል ሸበላ ሆኜ ምናምን ሳይሆን ተግባቢና ለሰው የምመች አይነት አድርጌ ራሴን ስለማቀርብ ይመስለኛል።እና ጥያቄዬ እስካሁን በዛ መልኩ ላስበው የቻልኩት ወንድ አለመኖሩና የሌሎቹንም ጥያቄ እንደጓደኞቼ የመቀበል ፍላጎት ባያድርብኝ ምንድነው ችግሩ? እስካሁን single ሆኖ መቆየቴ የተለየ ነገር ነው?
Oct 29, 2022አይ እህትነት . . . . . .በቃ ሁሉም ሰው Singleነትን እንደተለየ ነገር መቁጠሩ ይገርማል። እኛም ሲንግል ነን። ብዙ ጊዜ የተሻለ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች Single ናቸው። ( ከመጥፎ ቆጥሬው አደለም ) ለምን ብትይኝ? መጀመሪያ ለአላማቸው ቅድሜያ ይሰጣሉ። በTg ና በFb አበባ መለላክን እንደቁም ነገር አይቆጥሩም 😁 እና አላማ ካለሽ አላማሽን ለማሳካት በጥንቃቄ ተራመጂ እርሱንም አስቀድሚ! አማኝ ከሆነሽ በሃማኖትሽ ጠንካራ ለመሆን ተበራቺ። በመጨረሻም ሲንግለትሽን ወደጂው ብዙዎች ዳግም ሊመልሱት ማይችሉትን ነገር አድርገዋልና። አንቺ ደግሞ ምርጫ አለሽ . . . ብዙ ነገሮችም ያስተምሩሻል ብየ አምናለሁ። ይሔው ነው! ደና ሰንብቺ 👋😐
Oct 30, 2022