ሰላም እንዴት ናቹህ፡፡እኔ አሁን የማልፈልገዉ ትዳር ዉስጥ ነዉ ያለሁት፡፡ባለቤቴ ከእህቷ ጋር ሴራ ሰርታ ሳታረግዝ አረገዝኩ ብላ ነዉ ያገበዋት፡፡የሰርጋችን አካባቢ ፅንሱ ወረደ አሉኝ፡፡እህቷ ጋራ ትንሽ ጊዜ ሰንብታ መጣች፡፡ማግባቷን ስታረጋግጥ አረገዘች፡፡ ሁሉን ነገር ሴራዉን የሰማዉት በአዲስ አመት 2015 ነዉ፡፡አሁን ለይ ነፍሰ ጡር ነች፡፡እኔ እህቷንና ቤተሰቧን አምኜ ነበር ሳላስመርምር ያረገዘች መስሎኝ የተቀበለኩት፡፡ቤተሰቧን በሙሉ ጠላሁት፡፡ድሮዉን ሳልፈልግ ስላገባኋት እንጨቃጨቃለን፡፡አሁን ደግሞ ባሰብኝ እሷን ማየት አልፈልግም፡፡ምን ማድረግ እንዳለብኝ ምክር ብትለግሱኝ? እንዴት ነዉ መለያየት የምችለዉ?
Oct 28, 2022ጥያቄ፡- ሰላም ዶር እንዴት ነህ ሰለምትሰጠን ትምህርት በጣም ነዉ የማመሰገነዉ፡፡እኔ አሁን የማልፈልገዉ ትዳር ዉስጥ ነዉ ያለሁት፡፡ባለቤቴ ከእህቷ ጋር ሴራ ሰርታ ሳታረግዝ አረገዝኩ ብላ ነዉ ያገበዋት፡፡የሰርጋችን አካባቢ ፅንሱ ወረደ አሉኝ፡፡እህቷ ጋራ ትንሽ ጊዜ ሰንብታ መጣች፡፡ማግባቷን ስታረጋግጥ አረገዘች፡፡ ሁሉን ነገር ሴራዉን የሰማዉት በአዲስ አመት 2015 ነዉ፡፡አሁን ለይ በዚህ ወር ትወልዳለች፡፡እኔ እህቷንና ቤተሰቧን አምኜ ነበር ሳላስመርምር ያረገዘች መስሎኝ የተቀበለኩት፡፡ቤተሰቧን በሙሉ ጠላሁት፡፡ድሮዉን ሳልፈልግ ስላገባኋት እንጨቃጨቃለን፡፡አሁን ደግሞ ባሰብኝ እሷን ማየት አልፈልግም፡፡ምን ማድረግ እንዳለብኝ ምክር ብትለግሰኝ? እንዴት ነዉ መለያየት የምችለዉ? መልስ፡- በመጀመሪያ ይህ የገለጽከው ታሪክ በእርግጥም ሆኖ ከሆነ እንደዚህ አይነት ተግባር መፈጽመ ተገቢ ያለመሆኑን ነገር ጠቀስ አድርጌ ልለፍ፡፡ ወደአንተ ስመለስ ግን በሆነው ነገር ላይ የፍቅረኛህ እጅ የመኖሩና ትክክል አለመሆኗ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከሃላፊነት ግን ራስህን ማግለል አትችልም፡፡ ለማለት የፈለኩትን ግን ላብራራ፡፡ ከፍቅረኛህ ጋር የፍቅር ግንኙነት የጀመርከው ፈቅደህ ነው፡፡ ከእሷ ጋር ከጋብቻ በፊት ወሲባዊ ግንኙነት ውስጥ የገባኸው ፈቅደህ ነው፡፡ ከዚያም ጸንሻለሁ ስትልህ ያንንም አምነህ የተቀበልከው ፈቅደህ ነው፡፡ ጸነሰችም አልጸነሰችም በዚያ ማስረጃ ባልነበረው መረጃ መሰረት ወደ ጋብቻ የገባኸው ፈቅደህ ነው፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ላይ አተኩሬ የምነግርህ ያለህን ሃላፊነት በሚገባ እንደትገነዘበው ነው አንጂ ጨክኘብህ ወይም አንተን ብቻ ተጠያቂ ለማድረግ አይደለም፡፡ ያለፈውን የምርጫ ሃላፈነትህን ስትቀበል የሚቀጥለውን እርምጃህን በጥንቃቄ እንድታደርገው ሰፊ ምልከታን ይሰጥሃል፡፡ 1. ከሁሉም በፊት ያንን “ሴራ” ብልህ የጠራኸውን ነገር በእርግጥም ማድረጋቸውንና ታሪኩ እውነት መሆኑን መቶ በመቶ እርግጠኛ ሁን፡፡ 2. በእርግጥም እንደዛ ካደረገች፣ ብቻችሁንም ሆነ ከሰዎች ጋር ፊት ለፊትና በግልጽ ያህን ስሜት መንገርና የምትሰጥህን ምላሽ መስማት አስፈላጊ ነው፡፡ 3. ጥፋቷን ካመነችና ይቅርታ ከጠየቀችህ ይቅርታ ማድረጉ የሚጠቅመው ለራስህው እንደሆነ በማስታወስ ይቅርታ አድርግላት፡፡ 4. የመጨቃጨቃችሁ ሁኔታ በሁሉም ትዳር ውስጥ ያለ ነገር እንደሆነ አትርሳ፡፡ እየተዋደዱና አምነውበት ገብተውበትም የሚጨቃጨቁ ባለትዳሮች ብዙ ናቸው፡፡ 5. ለማንኛውም ግን ለፍቺ ከመቸኮልህ መረጋጋትና ጊዜ መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/ 🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔
Oct 28, 2022