Hey What do you do when your anxiety became severe? Suicidal thoughts are in mind pleas help😔
Oct 22, 2022ፈጣሪህ ስጋህ ውስጥ ነፍስ የዘራው አንተ እንድታጠፋው አይደለም። ፈጣሪህን አታስቆጣው። ራስን ማጥፋት በምንም ምክንያት ሰዋዊ ባህሪ አይደለም! ራስን ከሚያጠፉ ነገሮች መጠበቅ ነው የሰው ባህሪ። አስታውስ ይህም ቀን ያልፋል። የኔን ልንገርህ.. መሐል ከተማ ድልድዮችን ስሻገር ከድልድዩ ራሴን መወርወር የሚያሰኘኝ ጊዜ አሳልፌያለሁ። የሚገርመው ዛሬ ላይ ሆኜ ራሴን ላጠፋ የፈለግኩበት ምክንያት የሞኝ ምክንያት ነበር። በቢላዋ የደም ስሬን ለመቁረጥ የሞከርኩበትም ጊዜ ነበር። ግን ሲያልፍ ራሴን ወቅሻለሁ። ይህ ሁሉ ሰይጣን በውስጣችን ላይ የሚስልብን ክፉ ሐሳብ ነው። ባይሆን ስፖርት ጀምር። መፅሐፍ አንብብ። ምንም አይዋጥልህ ይሆናል። ግን አድርገው። አንድ ሆስፒታል ገብተህ የታመሙ ሰዎችን ጎብኝ። ተስፋ የሌላቸው ሞትን እየጠበቁ ያሉ ብዙ ህመምተኞችን ታገኛለህ። ለመሽናት፣ ለመንቀሳቀስና ለመተንፈስ የሰው እገዛ ያላቸውን ተመልከት። ነፍስን የመሰለ ነገር በውስጥህ ላይ የዘራልህ ፈጣሪህ እያየህና አብሮህ እንደሆነ አስብ። #የዛሬ_መጥፎ_ፈተና_የነገ_ምርጡ_ትውስታችን_ነው። አይዞህ ሐቢቢ ሁሉም ያልፋል። ፈጣሪህንም ታመሰግናለህ።
Oct 22, 2022