20 amete nw ወንድ first year ተማሪ ነበርኩኝ እና ለስራ ብዬ ሬጉላሩን ትምህርት ትቼ weekend ena የማታ ለመማር ወስኜ ነበረ ። ሀሳቤ እየሰራሁ ለመማር ነው እና እናቴ በእኔ ሀሳብ ተስማምታለች አባቴ በተቃራኒው በጣም ተናዷል ፣ሊያናግረኝ ፍቃደኛ አይደለም 6 ወር +++...ዘግቶኛል ምን ላድርግ ?? ለሰውም ቦዘኔ እንደሆንኩ ይናገራል በእኔ ቦታ ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር??የመጀመርያ ልጅ ነኝ ። አመሰግናለሁ
Oct 20, 2022This might be an odd answer but lemme say it. የአባትህ አቋም ትክክል ነው፥ የኔ አባትም ቢሆን እንዲሁ ያደርግ ነበር፣ So do I. ለሥራም ይሁን ሌላ ነገር ጊዜ አለው። አባትህ በዚ እድሜክ የሚፈልገው እንድትማርለት እንጂ ገንዘብ እንድታሳድድለት አይደለም። ምንም ያህል ሰርተህ ቢሊየነር ብትሆን ራሱ ትምህርት ከሌለህ አባትህን ልታስደስት አትችልም። ገና 20 ዓመትህ ነው፥ የሚያበሉህን አላጡም። ተማር፣ ለወግ ለመዓረግ ከበቃ በኋላ ሥራ። መሆን ያለበት በጊዜው ካልሆነ መቼም ትክክል አይሆንም። ገብሬ ራሱ መሆን ብትፈልግ ግብርና ተምረህ እረስ እንጂ ትምህርት አቋርጠህ ማረስ አእምሮውን ለገበረልህ አባትህ ድካሙን በዜሮ ማባዛት ነው። Just ወደ ትምህርትህ ተመለስ እና መማር የምትፈልገውን ተማር።
Oct 21, 2022