Selam Wendoch v yalhonech set btagebu mn ysemachuhal? Beteley muslim wendoch btmelsulgn des ylegnal
Oct 20, 2022ዘመኑ ላይ እንዳለ ወጣት ሊደብረን ይችል ይሆናል። አመዛዛኝ ለሆነ ወጣት ግን ለብጣሽ ስጋና ደም ያን ያህል ቦታ አይሰጠውም። ይህን ስል ሁሉም ሴት ከማንም ጋ ተጋድማ መጥታ ታግባ እያልኩ አይደለም። የሰው ልጅ ተሳሳች ወንጀለኛ ነው። ወንጀል ሰርታ ወደ ፈጣሪዋ በተስፋ ከተመለሰች አላህ ይምራታል። ሰውየውም አስተዋይ ከሆነ እሷ ብቻ ወንጀለኛ እንዳልሆነች ስለሚረዳ ይቅር ይላታል። የፈለገውስ ድንግልናዋን ነው ወይስ ኢማኗን፣ ቤተሰቧን፣ ውበቷን፣ ሀብትና ዝናዋን..? እንዳገባሽ ሰው እይታው ይለያያል። ከወንጀሏ ሳትመለስ የፈለገችውን እያተራመሰች ኖራ ለትዳር እኔ ጋ ብትመጣ ግን 'ኖ' ነው የምላት! እዛው በለመደችው። በተለይ የሚያበሳጨው ድንግል ሳትሆን "ነኝ" ብላ ዋሽታው ቢጋቡ ነው። ይህ ያሳምማል።🤦🏽♂ እሱ ለወደፊቱ አስቦ ራሱን ከስሜቱ አቅቦ ኖሮ አግብቶ እንደፈለገች የዘለለችን ሴት ማግባትም ለንፁህ ወንድም ህመም ነው። አግብታ የፈታች እንደሆነች እሱም ድንግልናዋን አይጠብቅም። ወይ ሊረዳት ወይ ሊማርባት/ሊያስተምርባት ነው ያገባት። በአጭሩ ለዚህ ዘመን እንደ ነብር ደም ለጠማው ወንድ ድንግል ላልሆነች ሴት ብዙ ደስተኛ አይገኝም። በዘመናችን ብዙዎቻችን ኢስላምን ሳይሆን በአላህ ያላመኑ ካፊሮችን አርዓያ አድርገን ይዘናል። ይህ ደግሞ የራሱ ተፅዕኖ አለው። ስንመክራችሁ አትሰሙን። አሁን ደግሞ ስታዝኑ እያየን እንዴት እንጨክን.. ባለጌ ወንድ የፈለገውን ሴት እንደፈለገ አጨማልቆ ከርሞ ለትዳር የሚፈልጋት ሴት ልቧም ሰውነቷም ያልተነካካውን ነው። አንቺን ተጠቅሞ ይጥልና ሌላ ንፁህ የሆነችውን ፍለጋ ይኳትናል። አላህ ሁላችንን ከወንጀል ሁሉ ይጠብቀን።
Oct 21, 2022