ወሒድ የንጽጽር ማኅደር: ተሀጁድ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 73፥2 ሌሊቱን ሁሉ ጥቂት ሲቀር ቁም። قُمِ اللَّيْلَ إِلَّا قَلِيلًا "ተሀጁድ" تَّهَجُّد የሚለው ቃል "ተሀጀደ" تَهَجَّدَ ማለትም "ተነሳ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መነሳት" ማለት ነው፥ ተሀጁድ በቁርኣን ውስጥ ተጨማሪ ሶላት ነው፦ 17፥79 ከሌሊትም ለአንተ ተጨማሪ የኾነችን ሶላት በእርሱ በቁርኣን ስገድ፡፡ ጌታህ ምስጉን በኾነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል፡፡ وَمِنَ اللَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِ نَافِلَةً لَّكَ عَسَىٰ أَن يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًا مَّحْمُودًا እዚህ አንቀጽ ላይ "ስገድ" ለሚለው የገባው ቃል "ተሀጀድ" تَهَجَّدْ ሲሆን "ተነስ" ማለት ነው፥ "ተሀጁድ" تَّهَجُّد የሚለው ቃል በግልጽ በሐዲስ ላይ መጥቷል፦ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 19, ሐዲስ 17 ሑዘይፋህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" ከሌሊት ተሀጁድ በሚቆሙበት ጊዜ በሢዋክ ጥሳቸውን ያነጹ ነበር"። عَنْ حُذَيْفَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ إِذَا قَامَ لِلتَّهَجُّدِ مِنَ اللَّيْلِ يَشُوصُ فَاهُ بِالسِّوَاكِ. "ቂያሙል ለይል" قِيَام اللَّيْل አጠቃላይ የሌሊት ሶላት የሚያመለክት ሲሆን ሌሊቱን ጥቂት ሲቀር የሚቆም ነው፥ ቂያሙል ለይል ሶላትን መቆም፣ ቁርኣን መቅራት እና ዚክር ማድረግ የሚይዝ ነው። የሌሊት መነሳት እርሷ ሕዋሳትን እና ልብን ለማስማማት በጣም ብርቱ ናት፥ ለማንበብም ትክክለኛ ናት፦ 73፥2 ሌሊቱን ጥቂት ሲቀር ቁም። قُمِ اللَّيْلَ إِلَّا قَلِيلًا 73፥3 ግማሹን ቁም ወይም ከእርሱ ጥቂትን ቀንስ፡፡ نِّصْفَهُ أَوِ انقُصْ مِنْهُ قَلِيلًا 73፥4 ወይም በእርሱ ላይ ጨምር፡፡ ቁርኣንንም በዝግታ ማንበብን አንብብ፡፡ أَوْ زِدْ عَلَيْهِ وَرَتِّلِ الْقُرْآنَ تَرْتِيلًا 73፥6 የሌሊት መነሳት እርሷ ሕዋሳትን እና ልብን ለማስማማት በጣም ብርቱ ናት፡፡ ለማንበብም ትክክለኛ ናት፡፡ إِنَّ نَاشِئَةَ اللَّيْلِ هِيَ أَشَدُّ وَطْئًا وَأَقْوَمُ قِيلًا ሙተቂን የሚባሉት የአሏህ ባሮች በጀነት ውስጥ የሚሆኑት ሙሕሢኒን ስለሆኑ ነው። ሙተቂን ከሌሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበሩ፥ በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ፦ 51፥15 አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ 51፥16 ያንን ጌታቸው የሰጣቸውን ተቀባዮች ኾነው በገነት ውስጥ ይኾናሉ፡፡ እነርሱ ከዚህ በፊት መልካም ሠሪዎች ነበሩና፡፡ آخِذِينَ مَا آتَاهُمْ رَبُّهُمْ ۚ إِنَّهُمْ كَانُوا قَبْلَ ذَٰلِكَ مُحْسِنِينَ 51፥17 ከሌሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበሩ፡፡ كَانُوا قَلِيلًا مِّنَ اللَّيْلِ مَا يَهْجَعُونَ 51፥18 በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ وَبِالْأَسْحَارِ هُمْ يَسْتَغْفِرُونَ የአልረሕማንም ባሮች በቂያሙል ለይል ለጌታቸው በግንባራቸው ተደፊዎችና ቋሚዎች ኾነው የሚያድሩት ናቸው፦ 25፥63 የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት እና ባለጌዎችም በክፉ ባነጋገሩዋቸው ጊዜ ሰላም የሚሉት ናቸው፡፡ وَعِبَادُ الرَّحْمَـٰنِ الَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى الْأَرْضِ هَوْنًا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ الْجَاهِلُونَ قَالُوا سَلَامًا 25፥64 እነዚያም ለጌታቸው በግንባራቸው ተደፊዎች እና ቋሚዎች ኾነው የሚያድሩት ናቸው፡፡ وَالَّذِينَ يَبِيتُونَ لِرَبِّهِمْ سُجَّدًا وَقِيَامًا ቂያሙል ለይል ከመተኛታችን በፊት እና ተኝተን ከተነሳንበት ያለውን ሶላት ሊያመለክት ይችላል፥ ተሀጁድ ግን ከእንቅልፋችን ተነስተን ሌሊቱን የምንቆመው ሶላት ነው። "ተራዊሕ" تَرَاوِيح ደግሞ በረመዷን ከዒሻእ በኃላ ከሌሊቱ የመጀመሪያው ክፍል የሚሰገድ ሲሆን ቂያሙል ረመዷን ነው፥ ተሀጁድ ከሌሊቱ ግማሽ ወይም መጨረሻ ሲሰገድ "ሶላቱል ለይል" صَلاَةُ اللَّيْل ነው፦ ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 48 ሐዲስ 210 አቡ ኡማህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ ዐምር ኢብኑ ዐበሣህ ነቢዩ"ﷺ" ሲናገሩ ሰምቶ እንደነገረኝ እርሳቸው እንዲህ አሉ፦ "በሌሊቱ የመጨረሻ ክፍል ጌታ ለአምላኪው ቅርብ ነው"። قَالَ سَمِعْتُ أَبَا أُمَامَةَ، رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ يَقُولُ حَدَّثَنِي عَمْرُو بْنُ عَبَسَةَ، أَنَّهُ سَمِعَ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ " أَقْرَبُ مَا يَكُونُ الرَّبُّ مِنَ الْعَبْدِ فِي جَوْفِ اللَّيْلِ الآخِرِ
Oct 19, 2022