ሰላም...መቼም ስድባችሁ አይቻልም ግን እስኪ1 ጥያቄ ልጠይቃቸችሁ ባለትዳር ነኝ እና ግን ልጅ እምቢ ካለን ቆየን ችግሩ ከሱ ይሁን ከኔ ወይ በጊዜው ፈጣሪ አልፈቀደ ይሁን አላወቅንም ግን በዚ ምክንያት መሰለቻቸት መደባበር ጀመርን አብረን ነው የምንኖረው ግነ አብረን አይደለንም ..ሁለታችንም ከስራ ገብተን በየፊናችን እንኖራለን ብቻ ትዳር አትበሉት በመሀል ስራ ቦታ ካለ ልጅ ጋር እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ግንኙነት ጀመርኩ በጣም ቸግባባን የባሌን ክፍተት የሸፈነልኝ መሰለኝ አብረን መዋል ማደር ጀመርን ..ከሱ ጋር ባደርኩ በሁለተኛው ቀን ባሌ ለስከዛሬው ነገር ሁሉ የይቅርታ አይደገምም ብሎ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ጠበቀኝ በሰአቱ ከሱ ጋም...ልክ እንዳልሰራሁ አውቃለሁ በመሀል በተፈጠረው ክፍተት ስህተት ሰርቻለሁ..ግን አሁን ግራ የሆነብኝ ነገር ተፈጠረ እስከዛሬ ስንፈልገው ያልመጣው ልጅ የ 2ወር ፅንስ ሆኖቁጭ እራሴም ሰርፕራይዝ ሆኛለሁ ግን ልጁ የማንኛው እንደሆነ ማወቅ አልቻልኩም በዚ ምክንያት ውዝግብ ብያለሁ ምን ይሻላል🤔 ምን ትሉኛላችሁ ልጁስ የማንኛው ይመስላችኋል??
Oct 15, 2022ባልሽ ሲያሳዝን! ልጅ ፈልገሽ ከሆነ ያገባሽው ልጅ የሰጠሽን አግቢ። በግልጽ ቋንቋ፥ ባልሽን እውነቱን ይወቅና ይቁረጥለት። ችግሩ ውሽማ ያፋታል እንጂ አያገባም።
Oct 19, 2022