ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ዛሬ የናንተን ምክር እና አስተያየት እሻለሁ እና የተወሰነ ነገር በሉኝ እስኪ መግለፅ ከምችለው በላይ የማፈቅራት ሴት አለች እና እሷ አሁን ባለችበት ሁኔታ ፍቅር የሚባል ነገር መጀመር አትፈልግም እንደምትወደኝ ነገራኛለች ልታጣኝ አትፈልግም ሁሌ ከጎና ልታየኝ ትፈልጋለች ግን ፍቅር የሚባለውን ነገር ማዘግየት ትፈልጋለች ስለፍቅር ስታስብ ትፈራለች ውስጧ ይረበሻል ምናምን ምክንያቱም በውስጡ አልፋበት ስለነበር ነው እና Break up ተፈጥሮ ብዙ ነገር አልፏል ግን አሁን ይዬንን ነገር መጀመር አልፈለገችም እናንተ ምን ትመክሩኛላችሁ አትወደኝም አትፈልገኝም ብዬ ሳስብ እወድሃለሁ እፈልግሀለው ትለኛለች እንደገና ደሞ እኔ ፍቅር ሊይዘኝ አይችልም ምናምን ትለኛለች እና ምን ላድርግ ልታጣኝ ካልፈለገች እንድርቃት እንድተዋት ካልፈለገች ለኔ የሆነ ስሜት አላት ማለት ነው??? በቃ አትፈልገኝም ብዬ ለቀቅ ሳደርጋት ጠበቅ አድርጋ ትይዘኛለች እና መልሼ ትኩረት ስሰጣት ለቀቅ ታደርገኛለች ምን ላድርግ? እኔ እንዳገባት ራቅ ወዳለ ቦታ ይዣት እንድጠፋ አብራኝ መኖር እንደምትፈልግ በኔ ደስተኛ እንደሆነች ትነግረኛለች እና አሁን በጣም ውዝግብ ብያለሁ ምን ላድርግ ዝም ብዬ ልጠብቃት ወይስ ምን? እሷ ማለት አለሜ ናት ህይወቴ ናት ከምላችሁ ከምትገምቱትም በላይ አፈቅራታለሁኝ እና የኔ እንድትሆን እፈልጋለሁ ሀሳባችሁን ስጡኝ አመሰግናለሁ።
Oct 08, 2022አንተን መፈለጓ ጥሩ ነገር ሆኖ፣ ነገር የዃላ ታሪኳ እየታወሳት ይረብሻታል። እንደ በፊቱ የሚሆን ይመሥላታል። ስለዚህ ባንተ ፍቅር እርግጠኛ አርጋት ፣ ከቃላት ይልቅ በተግባር ፍቅርህን አሣያት ተንከባከባት። የበፊት ቁስሏን ከሚቀሰቅሱ ነገሮች አርቃት፣ ወሬም ቢሆን ስለሡ የምታወራ ከሆነ ቀስ በቀስ አስቁማት። በተቻለ መጠን ብዙውን ጊዜ ከጎኗ አትለይ።
Oct 09, 2022