ከሁሉም በፊት አስቀድሞ በመጀመሪያ ከእስያ ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ የገብ ሀገሪቱም ይዘው የነበሩ ነገደ ኦሪ የተባሉት ናቸው ፡፡ የእነዚህም አባት በክብረ ነገስታት እደተፃፈው ከአዳም ልጆች አንዱ ኦሪ እደሆነ ያስረዳል፡፡ ከዚህ 21ነገስታት እንደነገሱ ይገልፃል ፡፡ ከዚህም በኃላ በመጨረሻው ንጉሣቸው በሶሊማን ታጊ ጊዜ በኖህ ዘመን በመጣው የጥፋት ውሀ መንግስቱ ወደቀ፡፡ የነዚህ ህዘብ ና ነገስታት ታሪክ ለማግኘት ክብረ ነገስት ላይ ሰፍሮ ይገኛል ፡፡ የነዚህ ነገስታት ሥም ዝርዝር የነገሡበት አመት እንመልከት ፡፡ 1,ኦሪ-60 አመት 2,1ጋርያክ-66 አመት 3,ጋንካም-83 አመት 4,ንግስት ቦርሳ-67 አመት 5,2ጋርያክ-60 አመት 6,1ጃን-80 አመት 7,2ጃን-60 አመት 8,ሰነፍሩ-20 አመት 9,ዘናብዛሚን-58 አመት 10,ሳህለን-60 አመት 11,ኤላርያን-80 አመት 12,ኒምሩድ-60 አመት 13,ንግሥት ኤልሉካ-45 አመት 14,ሳሉግ-30 አመት 15,ኀሪድ-72 አመት 16,ሆገብ-100 አመት 17,ማካውስ-70 አመት 18,አሳ-30 አመት 19,አፋር -50 አመት 20,ሚላኖስ-62 አመት 21,ሶሊማን ታጊ-73 አመት ከመራ በኃላ የጥፋት ውሀ ደረሰ ጊዜ በምድር ላይ ያለው ህይወት ከኖህ ቤተሰቦች
Oct 06, 2022