#relationships እንዴት ናቹ please እስቲ አማክሩኝ ሠፈር የማውቀው አንድ ልጅ አለ እና በፊት በፊት normal የአይን ሠላምታ ብቻ ነበረን እና ካዛ ግን እሱ ከእኔ ጋር ማውራት ይፈልጋል ሠፈር ሲያገኘኝ ስልኬን ከአንዴም ሶስቴ ጠይቆኝ አልሠጠሁትም ነበር (ሊያወራኝ ሲሞክር ቸኩላለው በኋላ ምናምን ብዬ ሠበብ ፈጥራለዉ)እንደዚህ የማደርገዉ ግን ልጁ የሚጠላ ሆኖ አይደለም ቆንጆ ረጅም እና ሚገርም አቋም ያለዉ ሠው ነው ፀባዩን ባላውቅም....ላወራው ያልፈለኩት ሠፈር አብሮ የሚውላቸው 2 ሠዎች አሉ እነሱን ስለምጠላቸው እንዲሁ ደብሮኝ ነበር እሱ ግን ተስፋ አይቆርጥም እሱ ባለበት መንገድ የምመጣ ከሆነ ዝናብ እየዘነበ ቆሞ ጠብቆኝ እንዳዋራዉ እና ስልኬን አንድሠጠው ጠይቆኝ ያውቃል ግን እኔ ስሜት ስላልነበረኝ ሠበብ ፈጥሬ አለፍኩት በሌላ ቀን በአጠገቡ ሳልፍ ዝም አለኝ ዞር ብሎም አላየኝ ከዛ ግን ካለፈ በኋላ ዞሬ ሳያው እሱም ዞሮ እያየኝ ነበር ግን ከዛን በኋላ ከሱ ፍቅር ያዘኝ በጣም ከባድ ፍቅር ጌታን ላገኘው ፈለኩኝ ግን ሠፈር ስለሆነ አጋጣሚ ነዉ የሚያገናኘን እኩል ሠፈር ካልወጣን በቀር አንገናኝም የት እንደሚሠራ አላውቅም ብቻ እሱ እንደዛ ሊያወራኝ ሲሞክር ያደረኩት ነገር ቆጨኝ በተለይ ደግሞ የዝናቡ ቀን.....ፍቅር በጣም ከባድ ነው
Sep 27, 2022እሺ
Sep 28, 2022