እኔ የምለው ድግሪ ይዞ ጥበቃ የሚቀጠርበት ሀገር ከኢትዮጰያ ሌላ የት አለ እእ አረረ መረረን በየት እንሽሎክ እስኪ ህይወት ላይ አማራጭ ካለቹ ወዲ በሉን ስራ ስናመለክት የሚጠራ የለም ሁሉም fake እስኪ መንገድ የምታውቁ ምሩን
Sep 26, 2022ተመርቄ ወደ ስራው አለም ከተቀላቀልኩ 7 ወር አካባቢ ይሆነኛል:: በህይወቴ አልፍበታለሁ ብዬ በማላስብበት መንገድ እያለፍኩ ነው:: ዲግሪ እና ማስተርስ እኛ ሀገር ላይ ልክ እንደ ኑሮ ውድነቱ ዋጋ ካጡ ነገሮች መሀል የሚጠቀሱ ናቸው (ለኔ):: 30 ቀን ሰርቼ በሚከፈለኝ ገንዘብ አይደለም ቤተሰብ መስርቼ መኖር እሁድ እንኳን ሻይ ቡና ለማለት ተሳቅቄ ነው:: (እግዚአብሔር ይመስገን ቢያንስ ቤተሰብ አለ : ቤተሰብ ጋር የማይኖር ተከራይቶ የሚኖር ሰውን መከራ እንዴት እጥፍ እንደሚሆን አስበው) ...እንደውም ህይወት fair እንዳልሆነች በምን ላሳይክ መሰለህ..እኔ የምሰራበት ቦታ አንድ ፅዳት ላይ የሚሰራ ልጅ አለ እና እንደዚሁ አንድ ቀን ስንጫወት መቀሌ ዩኒቨርስቲ እና እዛው መቀሌ ኮሌጆች ላይ ያስተምር እንደነበር ነገር ግን በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ወደዚህ መጥቶ አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃ ማግኘት ስላልቻለ ከዛ እስኪላክለት ድረስ የሰው አይን ላለማየት ጎንበስ ብሎ ያፀዳል:: አስበከዋል አለኝ ብለክ የምትመካበት ዲግሪ ቀርቶ ማስተርስ እንኳን ጥቅም አልባ ሲሆን??? ስለዚህ በአጭሩ ይሄን ልበልህ...ሁሉም መጨረሻው 1 ነው!!! ቆንጆ ስራ ኖረክም ጭራሽ ስራ አጥ ሆንክም ጉዞህ ወደ ሞት ነው:: በቻልከው አቅም አሁን ላይ ከቤተሰቦችህ ጋር አሳልፍ:: ደስተኛ የሚያደርግክን ነገር አድርግ!!! ህይወት ቀልድ ነው...ቃሉም እንደሚለው ላለው ይጨመርለታል : ከሌለው ላይ ግን ይወሰድበታል ነው:: እግዚአብሔር ነገ የተሻለውን ቀን እንዲያመጣ እየለመኑ ከመኖር ውጪ ምን ሌላ ምርጫ አለ???
Sep 27, 2022