ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። ትንቢተ ዕንባቆም 3 : 18
Sep 26, 2022ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። ትንቢተ ዕንባቆም 3 : 18
Sep 26, 2022Can't choose between this two ገመድ ባማረ ስፍራ ወደቀችልኝ፥ ርስቴም ተዋበችልኝ።" (መዝ 16: 6) Ena ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። Tmbite embakom ❤️❤️❤️
Sep 26, 2022Yemjmrya Andmtaw mndn nw Sle embetachen nw?
Oct 12, 2022…
Sep 26, 2022ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው ❤️
Sep 26, 2022ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሔር ይቻላል ። ሉቃስ 18:27
Sep 26, 2022.መንገድህን ሁሉ ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ
Sep 26, 2022ዕብራውያን 6፥10 እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።
Sep 26, 2022“ከፍታም ይሁን ጥልቀት፣ ወይም የትኛውም ፍጥረት፣ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።” — ሮሜ 8፥39 (አዲሱ መ.ት)😍😍😍
Sep 26, 20221ኛ፣ ነገር ሁሉ ለበጎ ነው። 2ኛ፣ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት እርሱ ስለናንተ ያስባለ እና
Sep 26, 2022ሁሉ በእርሱ ሆነ
Sep 26, 2022ዘዳግም 6 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤ ⁵ አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ። ⁶ እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ። ⁷ ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። ⁸ በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ። ⁹ በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው።
Sep 26, 2022ሮሜ 8 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁴ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። ¹⁵ አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። ¹⁶ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ¹⁷ ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን። እና ዮሐንስ 3 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ¹⁷ ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። ¹⁸ በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።
Sep 26, 2022በአንተ ታምኛለሁና፣ በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና፣ የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ። መዝሙር 143:8
Sep 26, 2022ውዴ የኔ ነው እኔም የሱ ነኝ ። የ ሰለሞን መዝሙር
Sep 26, 2022Ytibeb mejemra egzabern mefrat nw
Sep 26, 2022እግዚአብሔር ፍቅር ነዉ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ሁሉም ለበጎ ነዉ
Sep 26, 2022(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 124) ---------- 1፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል። 2፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥ 3፤ ቍጣቸውን በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፤ 4፤ በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ፈሳሽ ባለፈ ነበር፤ 5፤ በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር። 6፤ ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ። 7፤ ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች። ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን። 8፤ ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ በእግዚአብሔር ስም ነው።
Sep 27, 2022ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው። መጽሐፈ መክብብ 3 : 1
Sep 26, 2022መዝሙረ ዳዊት 91:2 እግዚአብሔርን፡— እርሱ መታመኛዬና መጠጊያዬ፡ አምላኬ ነው፡ እላለሁ።
Sep 26, 2022