#religion ዮሐንስ ወንጌል ላይ 16:26 "በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ እኔም ስለእናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም" ይህ ማለት ኢየሱስ አማላጅ አይደለም ማለት ነው??😳🙊 እስቲ አስረዱኝ ስላልገባኝ ነው😁
Sep 21, 2022👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆ጠያቂዋ ጥሩ ጥያቄ አንስተሻል በፁሁፍ ስላልሽ እየከበደኝም ቢሆን ልፃፍ መጀመሪያ አዳም ሲበድል እግዚአብሔርን ነው የበደለው አብ ወልድ ና መንፈስቅዱስን በጋራ ከዛ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለው ብሎ ቃል ሲገባለት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሊታረቁት እንደሚችሉ ተስፋ ሰጡት ከዛ ጊዜው ሲደርስ አንድያ ልጁን ወልድን ሲልክ ወልድ ተበዳይ በአዳም ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሆኖ የእርቅ መስዋእት ራሱ ለአብ ለመንፈስ ቅዱስና ለራሱ አቅርቦ እኛን ከአብ ከራሱ ጋ ከወልድ ና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስታርቆናል ይህንን ያደረገው እኛ ስላቃተን እሱ መሀሪ ስለሆነ ያንን እዳ መክፈል ሲያቅተን እራሱ ተበዳይ እራሱ ለራሱ ካሳ ከፍሎ ራሱ ታረቀን እንጂ እነሱ እንደሚሉት እኛ ና አብን አላስታረቀም እኛ ና እግዚአብሔርን እንጂ እግዚአብሔር ደሞ አብም ወልድም መንፈስ ቅዱስም ስለሆነ ወልድን ያማልዳል ካሉ ራሱን ለራሱ አማልዷል ማለት ካልሆነ በስተቀር አዳም አብን ብቻ እንደበደለ ና ወልድ ደሞ መሀል ቤት አስታራቂ ማስመሰል ነው ሚሆነው በመጨረሻም ከአብ ከመንፈስቅዱስና ከራሱ ጋር ማስታረቅን ጨርሶ የተቀረውን ማስታረቅ ለሐዋርያት ለፃድቃን ሰማዕታት እንደሰጡ ከታች ባለው ጥቅስ ተናግሯል 2ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 5ቁጥር 19 ጀምሮ 19እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። 20እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን። ስለዚሀ በምድር የነበረውን ማስታረቅ [ማማለድ ጨርሶ ከሱ በሃላ ለሐዋርያት ለተከታዮቹ ማማለድን ሰጥቷል ከነሱ በሃላ ደሞ ለተነሱ ታላላቅ አባቶች ፓትርያርኮች ከዛም ለፃድቃን ሰማዕታት ከሁሉም ምትበልጠው እመቤታችን ደሞ ይህ ለሷ ትንሹ ስጦታ ነው። ዳግም ደሞ ማማለድ በአምላክ እንደሌለ ሲገልፅ : ዮሐ ወንጌል 16÷15 አብና ወልደ እኩል እንደሆኑ ገፀታ ሲናገር ከዛ ቁጥር 23 ላይ አብን በስሜ ምትለምኑትን ይሰጣቹሀል ይላል ከዛ 26 ላይ ደሞ ስለናንተ አብን አልለምንላችሁም ይላል ስለዚህ ጌታ አያማልድም ፈራጅ እንደሆነ በሐዋርያት ሲመሰከር ለሕዝብም እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በእግዚአብሔር የተወሰነ እርሱ እንደ ሆነ እንመሰክር ዘንድ አዘዘን። የሐዋርያት ሥራ 10 : 42 ጌታ ፈራጅ ነው።
Sep 22, 2022