ሰላም እንዴት ናችሁ be alemawi sayhon be menfesawi bekul btmelsuligh specially Orthodoxawiyan andit set ye gabcha tyake lefkreghawa(lewendu) makreb weyim meteyek tchilalech wey ?behaymanotachin bekul chiger alew yihon setua bteyik ..lelaw ene yegziyabher fkadu bihon magbat yemfelgew be teklil nw am v ena esum yegid v mehon alebet aydel gin behone menged esu v bayhon mndnew yemihoneW? pls bekninet melsuligh 🙏ለመልሳችሁ አመሰግናለሁ
Sep 21, 2022የፍቅር ጥያቄውን በተመለከተ ከየትኛውም ወገን ቢመጣ ችግር የለውም። ፍቅርን ትዳርን ደስታን ሽታችሁ ፈልጋችሁ ስለሆነ የጋብቻ ጥያቄ የምታቀርቢው/በው ምንም ለውጥ አይፈጥርም። ድንግልና እና ጋብቻን በተመለከተ እኔ ድንግል ስለሆንኩ ባለቤቴ/እጮኛዬ/ፍቅረኛዬ የግድ ድንግል መሆን አለበት ማለት መብትሽ ነው። ሁለታችሁም ድንግልናችሁን ጠብቃችሁ ለጋብቻ ከበቃችሁ ቅድስት ቤተ ክርስትያን በስርዓተ ተክሊል (ካባ አልብሳችሁ ፣ አክሊል ደፍታላችሁ ፣ በቅዱስ ስጋ ወደሙ አክብራ) ጋብቻችሁን ባርካ ትድራችኋለች። ከሁለት አንዳችሁ ደግሞ ድንግልናው ከእርሱ ከሌለች ወይንም ደግሞ ሁለታቸውም ድንግል ባይሆኑ ቅድስት ቤተክርስትያን ካባ አልብሳ በቅዱስ ስጋ ወደሙ አክብራ እልልልልል ብላ ጋብቻችሁን ባርካ በስርዓተ ቁርባን ትድራችኋለች። (እዚጋር ልብ ማለት የሚገባን አንዳቸው ድንግል ሆነው አንዳቸው ባይሆኑ ቅድስት ቤተክርትያን "ድንግልናውን ለጠበቀው" ሰው ብላ መፅሐፈ ተክሊልን ደግማ አክሊል አትደፋለትም። ይልቁንም ድንግል የሆነው ሰው አክሊል መድፋት ሲገባው ድንግል ላልሆነው ሰው ሲል ስለ ፍቅር ሲል ራሱን ዝቅ አድርጎ በስርዓተ ቁርባን ጋብቻን ይመሰርታል። ክብሩን ዝቅ በማድረጉም ክርስቶስን ይመስላል በረከትም ያገኛል።)💚💛❤️
Sep 21, 2022