ይህ ጥያቄ ለሴቶች ነው በጣም የምወዳት ፍቅረኛ አለችኝ ምንም ነገር የምሆንላት። እሷም በጣም እንደምትወደኝ ትነግረኛለች ችግሩ ግን እኔ ለሷ የምሆንላትን እሩቡን እንኳን ለኔ አትሆንም በተለይ ብዙ ጊዜ ላግኝሽ ስላት መልሷ አይመቸኝም ነው ምክንያት ብላ የምትሰጠኝ ደግሞ የማያሳምን ብቻ ሳይሆን አስቂኝም ጭምር ነው ። እኔ እሷን ለማግኘት የማልፈነቅለው ድንጋይ የለም እሷ ግን እኔን ለማግኘት ምንም ጥረት የምታደርግ መስሎ እየተሰማኝ አይደለም። የምታፈቅረኝ ከሆነ ለምንድነው እንዲህ የምትሆነው?
Sep 18, 2022በሴቶች መዝገበ ቃላት የተጠሩበትን አላማ ለማሳካት ነብሳቸው ውስጥ በደማቁ የተፃፈ "ራስን ማዋደድ" እሚባል ትልቅ ነገር አለ። …ስትደውልላት አታነሳም፤ ቴክስት አትመልስም፤ ልታገኛት ስትልግ በጣም ብዙ ስራ አለባት😁 ወዘተ ነገር ግን በተገኘው አጋጣሚ እንደምትወድህ ካንተ ሌላ ወንድ ያለ እትደማይመስላት ትደሰኩርልሀለች ምናምን ግን ሁልጊዜ ከወሬ ተግባር የበለጠ ስለሚናገር… ኢሄን አርጋ ስለሷ አብዝተህ ማሰብ ከጀመርክ ቁማሩን ተበልተሀል! ንቃ! ንቃ!… በእርግጠኝነት እምነግርህ ነገር የምር ለምትወደው ሰው በቀን ቢያንስ 15ደቂቃ አታጣም። በጣም ቢዚ እሚያረጋት ነገር ካለም ለአንተም አሳማኝ ይሆናል የመገናኛ ጊዜውንም ራሷ ታመቻቻለች ግን ሴት ከሆነች ግን 0.1 ሰከንድም ላይኖራት ይችላል😜 So 2 የመፍትሄ አማራጭ። 1.እሷ በሄደችበት ሂድና ቁማሩን ብላት 2. እንደማቆያ ተቅመህ ትክክለኛዋን ፈልግ። የተፈጠርነው በሴት ርካሽ ቁማር ለመሰበር አይደለም! ቻው።
Sep 19, 2022