✅እንቁላል ከገበሬ ገዝተህ ማከፋፈክ ✅ቂቤ ከክፍለ ሀገር ምናምን አምጥተህ ለሱቆች ማስረከብ ✅ቡና ከክፍለ ሀገር አምጥተህ ለሱቅ ማስረከብ ✅ዶሮ ጫጩት ከጎጀብ ገዝተህ አሳድገህ በ2 ወር እጥፍ አትርፈህ መሸጥ ✅ ችግኝ ገዝተህ ቦታ ካለህ እያራባህ እያሳደክ መሸጥ ✅ የእንስሳ ቆዳ ከፍለ ሃገር እያመጣህ በገና ክራር ከበሮ ምናምን ለሚሰሩት ማከፋፈል ✅ ወተት ሱሉልታ ወይ ገላን እየገዛህ ማከፋፈል ቀስ በቀስ ያድጋል ✅ አዲስ አበባ ካለህ ከደስታ ስኬት ቦርድ በብድር እየወሰድክ ክፍለ ሀገር ሽጠህ ቀስ እያልክ ማደግ ✅ 4 ሊስትሮ እቃዎች አሟልተክ ጎዳና ላይ ያሉ ልጆችን አስተምረሃቸው ትርፍ የጋራ ቦታ ፈልገህ ማሰራት እነሱም ከልመና ወጡ አንተም ገቢ ታገኛለክ ✅ ብስኩት እየጠበስክ ለሻይ ቤቶች ማከፋፈል ✅ ቆሎ በትንሹ እያሸክ ለሱቆች በመሸጥ መጀመር ✅ የተማርክ ከሆንክ የማስጠናት ስራ ብትጀምር ብቻ ወርጄ ሰራለው ካልክ ስራ መች ጠፋ ሁሉም ከታች መነሳት ስለማይፈልግ እና ስለሚንቅ ነው እንጂ
Sep 18, 2022