ሰላም ሰዎች እኚህን ጥያቄዎች እባካችሁ ካወቃችሁ መልሱልኝ -ታኦዶኮስ ምን ማለት ነው እና ማነው ? -ጲላጦሰ በማን እጅ ተሰዋ ? ለመልሳችሁ አመሰግናለው 🙏🙏🙏
Sep 17, 2022ታኦዶኮስ፦ ብሂል" ዘውእቱ ወላዲተ እግዚአብሔር" ታኦዶኮስ የሚለው ቃል የፅርዕ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም "ዘውእቱ ወላዲተ እግዚአብሔር " ፦ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ቃል እናት ናት ማለት ነው ። ቅ/ቄርሎስ "እንደኛ ነፍስን ፣ሥጋን መዋሐዱ አንድ ክርስቶስን ድንቅ በሚያሰኝ ልደት በወለደችው ጊዜ ንጽሕት ድንግል ማርያም ታኦዶኮስ እንደሆነች እናምናለን ።ይኸውም አምላክን የወለደች ማለት ነው (" ሃይ.አበ.75፤37)።አምላክን በሌላ መንገድ ወለደች ብለን እንዳንጠራጠር እዚሁ ጥቅስ ላይ ቅ/ቄርሎስ "አምላክን የወለደች ናት ብንልም ንፅህት ድንግል ከሥጋ የተለየ መለኮትን እንደወለደች አድርጋችሁ መጠራጠር በልባችሁ አይደር ፤ ነፍስን ሥጋን የተዋሐደ የእግዚአብሔር ቃልን ወለደች እንጂ ፤ በዚህ በተዋሕዶ ምስጢር ብቻ እንጂ በሌላ አምላክን ወለደች አንልም " በማለት አጥብቆ ይናገራል ። የዚህ መሠረቱ እመቤታችን ገንዘብ እያደረገችው ንጽሕት የአዳም አካል ናት ።በቅ/ማርያም ላይ "ስፍሖ ገብረ ዘእምጥንተ ሥጋሁ ለአዳም "፦አካሉን መርገም ያልወደቀባት 7ቱን ዓመት በገነት የነበረ የአዳምን ሥጋ አደረገው"ሲል ሊቁ አባ ሕርያቆስ ያመሰጥረዋል። የአብ አካላዊ ቃል ወልድ ዋሕድ አዳም በድሎ ንስሀ በገባ ጊዜ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኀለሁ ብሎ በሠጠውን ቃል ኪዳንመሠረት ከላይ እዳየነው መሠረቱ(መጀመሪያው) በዚህ ምክንያትነውናእመቤታችንቅድስት ድንግል ማርያምን ታኦዶኮስ በማለት ቅ/ቄርሎስ ጠርቶታል ። የቤተክርስትያኗ ጌጥ የሆነው ቅ/ዮሐ/አፈ በድርሳኑ የወልደ ማርያምን አምላክነት የድንግልን እመ አምላክነት የማያምን አይሁዳዊን "ንግረኒእስኩ አይሁዳዊ ወዜንወኒ መኑዝ ዘወለደቶ ድንግል ወአጠይቀኒ ዘከመ አጠየቆ ለሄሮድስ አይሁዳዊ እስኪ ንገረኝ ድንግል የወለደችው ይህ ማነው? ለሄሮድስ እንዳስረዳኸው ለእኔም አስረዳኝ ፣ይገድለው ዘንድ ለርሱ ነገርከው እንጂ እሰግድለት ዘንድ ለእኔ ለምን አትነግረኝም? ድንግል የወለደችው ይህ ማነው? እርሱስ ፍጥረታትን ሁሉ የፈጠረ ጌታ ነው ። በማለት ለኢአማንነያኑ ሰዎች ሲገስፃቸው እናያለን ። በእውነቱ እነዚህን አባቶች ባያስነሳል ኖሮ መናፍቃን የሚያጎርፉትን ምንፍቅና መቋቋም ባልተቻለን ነበር ።ታዲያ እነዚህን ቅዱሳን አባቶች መናፈቅን አውግዘው ሃይማኖትን አቅንተው እነ ቅዱስ ቄርሎስ እመቤታችንን ታኦዶኮስ በማለት ጽኑዕ እምነት ሃይማኖት ማለትስ ወልደ አብ ወልደ ማርያም በተዋሕዶ ከበረ ብሎ ማመን መሆኑን ታኦዶኮስ በማለት አስረዳን ። እኛን ለፈጠረ ለእግዚአበሐር ፣ እመቤታችን ናመድኃኒታችን ለምትሆን አምላክን ለወለደች ለማርያምም፣ የድኅነታችን ዕፅ ለሚሆን ክርስቶስ ለተሰቀለበት መስቀሉም ምስጋና ይገባል ። አዘጋጅ ዲ/ን ጥላሁን በለጠ
Sep 18, 2022