Hi ሰላም ዛሬ ስለ ስራ እናዉራ እስኪ በተለይ መካከለኛዉ ላይ ያላችሁ ነጋዴዎች ካላችሁ ማለትም ከአስመጪዎች እቃ እየቀበልን ምታከፋፍሉ እና ምትቸረችሩ ሰዎች ካላችሁ የምር ግን የገብያዉ ሁኔታ እንዴት እየሆነላችሁ ነዉ? ማለት ሰዉ እንደ ስግብግብ ሚቆጠረን እኛን መካከለኛውን ነጋዴ ነዉ ካላይ ያሉ ነጋዴዎችን ሚናገር ህብረተሰብ ሆነ መንግስት የለም አንድ እቃ ዛሬ አስገብተህ ነገ ልትገዛዉ ስትሄድ የሃ እቃ እጥፍ ይጨመራል ያለህ አመራጭ ያለህን እቃ ከዋናዉ ቦታ በጨመረዉ ልክ ትሸጣለህ (እሱንም ገብያ ካለ) እዚ ያለዉ ሸማቹ አንተ ምትጨምር ይመስለዋል ገብያዉ ግራ ግብትብት ብሎታል በየጊዜዉ እቃዎች ዋጋቸው ይጨምራሉ እዚ በሸጥክበት ዋጋ ነዉ ቀጣይ ስትመጣ ምትገዛዉ ልፋቱ እና ስራዉ ትርፍ የትልልቅ ባለ ሀብቶች ሲሳይ ሆኗል ሰርተህ መለወጥ ማይታሰብ ነገር ነዉ ባጠቃላይ ገብያዉን ፉክክር አልባ ያደረገዉ ምንድነዉ? ገብያዉ የጥቂት ባለሀብቶች መጫወቻ ያደረገዉ ነገርስ ምንድነው?
Sep 17, 2022Awo ewnet new beyegizew waga mechemerun yemiasawkut etach yalu negadewoch nachew sewu demo awko yechemerebet eyemeselew yemiragemewm esun new gebiaw fukkr yataw demo free market yemibalew sletesfafa ymeslegnal hulum endeflagotu eyechemere yasrekbal mn ydereg
Sep 17, 2022