Muslims agzugn Smetachun metagel slcht bluachu ayawkm? There is tefetroawi attraction towards the opposite sex ena kesuga tgl beka wend simeta ayn mesber, menged mekeyer, lalemenekakat bota mekeyer, dmtsen endaysemut kes bye mawrat, aremameden kes mareg, beftsum ke wend ga alemawrat( asfelagi kalhone) all this shsht ena tgl having that attraction in my heart. Kemr skay honobgnal😭 Why r we given these feelings in the 1st place eshi? Bezi zemen yalew fitna yihe nw teblo migelets aydelem Ena tglu adkmuachu ayakm? Ene mnm smet endinoregn alfelgm Mkniyatum smetu wede haram enji wedetm aymeram Gn demo smet alegnenem miwesewsegn neger ale Yihen eyetagelu menor endet nw milemedew? Weym eskene mechereshaw endet nw smet alba mehon michalew? Any advise is appreciated especially related to our deen
Sep 16, 2022አስላም አለይኩም ስሜትን መታገል በጣም ትልቅ እና ከባድ ነገር ነው እህቴ አንቺ ደግሞ ተሳክቶልሻል እራስሽን ከሀራም ታድገሻል አላህ ካሰብሽውና ከተመኘሽው በላይ ኸይር ነገረ ይስጥሽ ብዙ ሰዎች በአላህ እርዳታ ተሳክቶላቸው እራሳቸውን ከመጥፎ ተግባር ማራቅ ችለዋል አላህ(ሱወ) ዝሙትን በቁርአን ሲከለክል ዝሙትን አትስሩት ሳይሆን ጭራሽ አትቅረቡት ነው ያለው እዚህ ላይ ልብ በይ ከ አጅነቢይ መራቅ በሁለታችሁ መሀል መላመድ መቀራረብ ከዛ ቀስ በቀስ ግኑኝነቱ ወደሌላ ነገር ከፍ እንዳይል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስለሚያደርግ ነው በዚህ ዘመን ራስን ከፊትና መጠበቅ በጣም አስቸጋሪ ነው ግን ደግሞ በአላህ እርዳታ ከ መጥፎ ነገር መጠበቅ ይቻላል 1, እድሜሽ ለትዳር ከደረሰ በማግባት 2, ለትዳር ዝግጁ ካልሆንሽ ኢባዳ በማብዛት ፆም በመፆም ወደ አላህ መቃረብ 3,ፊትናውን እንዲቀንስልሽ ዱዓ በማድረግ 4,አለባበሰሽን በማስተካከል 5,ፈልም ሙዚቃ tik tok የመሳሰሉት ስሜትን ስለሚያነሳሱ ከነሱ በመራቅ 6,ከጥሩ ጓደኞች ጋር ብቻ መሆን ከቀልቃሎች በመራቅ 7,የዲን ትምህርቶችን በቋሚነት በመማር ራስሽን ወደሚያስደስትሽ መንገድ መምራት ትችያለሽ ልብ በይ አንቺ ራስሽን በመጠበቅሽ ሌሎች ወንድሞችሽን ከፈተና ጠበቅሻቸው ማለት ነው አላህ ደግሞ ለጥሩ ሰዎች በጣም ጥሩ ሰዎችን አዘጋጅቷልና አንቺም ከፊትና መጠበቅሽን ጥሩ ባል ለማግኘት ቀብድ እከፈልሽ እንደሆ አስቢው በዙሪያሽ በዲኑ በዱንያው የወደድሺው ሰው ካለ ቶሎ ሽማግሌ ላክ በይው ይሄ ሀላል ነው አላህ ከምትጠይው ፊትና ይጠብቅሽ
Sep 17, 2022