ኧረ ሰዎች እርዱኝ በጣም አይነፋር ሴት የምፈራ የሆንኩ ሰው ነኝ እና የሆነች የክላስ ልጅ ወድጄ ፍቅሬን መንገር ተራራ ሆነብኝ ከልጅቷ ሁሌ በአይን እንተያያለን ግን አውርተን አናውቅም ። ዛሬማ አዋራታለሁ እልና ምን ብዬ እንደማዋራት አላውቅም በጣም እፈራለሁ😢 ። እሷ ደግሞ እናዳዋራት ትፈልጋለች እንዳዋራት ለእኔ ቅርብ የሆኑ ወንበሮች ላይ ትቀመጣለች እኔ እንኳን ላዋራት ወደኔ ስትቀርብ እጄ መንቀጥቀጥ ይጀምራል አፌ ይተሳሰራል🥺። እንደኔ የነበራችሁ ምን ላድርግ ? ምንስ ብዬ ወሬ ልጀምር እንደዚህ አይነት ችግር የሚፈታ መፅሀፍም ካለ ንገሩኝ እንደዚህ አይነት ነገር የመጀመሪያዬ ነው ወገን ኧረ ንገሩኝ😭😭
Sep 15, 2022ቅረባት በቃ ቀለል አድርገህ እንደ ጓደኛ እሷ ስለ አንተ ስሜት የምታቀው ታሪክ አለመኖሩን እና አንተ ቀርበክ ስለአወራካት ሌላ ነገር እንደማታስብ እራስክን ማሳመን አለብክ። ሁሉም ነገር ያለው በእራስክ እጅ ላይ ነው። ስሜትህን ተቆጣጥረክ ልክ እንደ ክፍል ጋደኛ ቅረባት ። የሆነ ቀን ክላስ ስትገባ ዝም ብለክ በድምፅ ብቻ ሰላም ብለካት እለፍ የሷን መልስ ሳትጠብቅ ከዛ ባቅራቢያዋ ተቀመጥ ከዛ በሌላኛው ቀን ሰላም ብለካት ከጎኗ ቁጭ በል በቃ ቀለል አድርገህ ስለ ክላስ ሳታበዛ ስለ ትምህርት ምናምን አውራት ። ፍርሀት እራስክ የምትፈጥረው ተራ ስሜት ነው። ከፈለክም ልታስወግደው ትችላለክ ይሔንን ማወቅ አለብክ። እኛ ሀበሾች ለሰው ከመጥፎ ስሜት ይልቅ ጥሩ ስሜታችንን ለመግለፅ እንፈራለን። ግን መሆን ያለበት የተገላቢጦሽ ነበር። ለሰው ጥሩ ስሜት ሲኖርክ ያንን ሰው ለማቅረብ እና የራስክ ለማድረግ ድፍረቱን እና ወኔውን ማግኘት አለበክ እንጂ ...የፍርሀት ስሜት እራስክን ከዛ ሰው ሊያርቅክ አይገባው። ስለዚህ የፍርሀት ስሜትክን ለማሸነፍ ከእራስክ ጋር ትንሽ መታገል አለብክ። አይዞን ታደርገዋለክው
Sep 16, 2022