1) የዮሐንስ ራዕይን የፃፈው ወንጌላዊው ነው መጥምቁ? ወይስ ሌላ ዮሐንስ አለ? የዮሐንስ መልዕክት የሚለውንስ ማነው የፃፈው? 2) የዮሐንስ ወንጌል ትርጓሜ መፅሀፍ ካለ ላኩልኝ ወይም ስሙን ንገሩኝ (የፓስተር ዮናታንን አልፈለግኩም ኦርቶዶክስ ነኝ) 3) የፀሎት መፅሀፍት ላይ ሊጦን ስለሚባለው ፀሎት ብትነግሩኝ:: መች መች እንደሚፀለይም:: 4) አንድ ሰው ለቤተክርስቲያን ማበርከት የሚችለው ምን አይነት መፅሐፍ ነው? ምሳሌ ብትሰጡኝ ደስ ይለኛል:: አመሰግናለሁ
Sep 14, 20221) ሁሉንም የጻፈው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው። ወንጌላዊው ዮሐንስ ግን ብዙ ሰሞች አሉት። -የዜብድዮስ ልጅ ዮሐንስ(ወልደ ዜብድዮስ) -ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ -ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ -ዮሐንስ ነባቤ መለኮት (ታኦሎጎስ) ተብሎ ይጠራል። 2) @eotcLIBRARY 3) ሊጦን በብዙ ቦታ ያልተለመደ ቢሆንም ከኪዳን ጸሎት በኋላ የሚጸለይ ጸሎት ነው። 4) የትኛውም መጻሕፍት መበርከት ይችላል። ቢቻል ቢቻል መጽሐፈ ዲድስቅልያ ቢገኝ መልካም ነው ብዙም ስለማይገኝ👀
Sep 14, 2022