Besides other reasons the very obvious one is commemorating the finding of the true cross by Queen Eleni.
Sep 28, 2020Besides other reasons the very obvious one is commemorating the finding of the true cross by Queen Eleni.
Sep 28, 2020Cause jesus got nailed
Sep 28, 2020It's the commemoration Nigist Eleni (Empress Helena of Rome) who found the of cross of Jesus Christ that was hidden under a damp by jews. She used a bon-fire to reveal the location of the cross( so the direction of the smoke will tell her the exact direction of the cross) ; which is why we celebrate damera by lighting a bon-fire. Here's the backstory of how she decided to find it: Queen Helena was married to an unbeliever, because it was hard at that time to find belivers, so Christians would marry people and convert them to their religon. She gave birth to Constantine, who happened to be the great emperor who was the religon was expand throughout Rome, but when he was young she prayed to God "if you make my son be a believer, i'll find your cross",, her will was fulfilled and she did. The reason we Ethiopians highly celebrate it is because we belive that half of the cross is found in Ethiopia. As for how it came, there is a story of how Emperor Dawit of Ethiopia was granted that cross by Egyptians in return to his huge efforts of fighting against prosecution Egyptian Coptic christians. I hope this helped ❤️
Sep 28, 2020Because jesus christ show her power all person
Sep 28, 2020You could have watched etv. Small pp
Sep 28, 2020Bro fr fr selechehegn try to come with more interesting questions
Sep 28, 2020Dn Yordanos Abebe (ገብሩ ለቅዱስ ዳዊት ) ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ✞✞✞ እንኩዋን #ለብርሃነ_መስቀሉ እና #ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ ✞✞✞ #ቅዱስ_ዕፀ_መስቀል ✞✞✞ =>ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ #ማርያም_እግዝእት በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ መከራ መስቀልን ተቀብሎ: ¤ከግራ ቁመት: ¤ከገሃነመ እሳት: ¤ከሰይጣን ባርነት: ¤ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል:: =>+"+ እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ +"+ እንዳለ ሊቁ:: +ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም ራሷ አርአያ #ትዕምርተ_መስቀል ናት:: +እግዚአብሔር ለቃየን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት (ዘፍ. 4:15) ጀምሮ ¤#ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት (ዘፍ. 22:6): ¤#ቅዱስ_ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል (ዘፍ. 28:12): ¤ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ (ዘፍ. 48:14): ¤ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው #የሙሴ_በትር (ዘጸ. 14:15): ¤#የናሱ_ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት (ዘኁ. 21:8) ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል:: +#ቅዱስ_ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል:: (መዝ. 59:4) +በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት:: ስለዚህም "#መስቀል_ብርሃን_ለኩሉ_ዓለም: #መሠረተ_ቤተ_ክርስቲያን" ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል:: +#ቅዱስ_ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን ይነግረናል:: #ብርሃነ_ዓለም #ቅዱስ_ዻውሎስም ስለ መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን ነውና:: (1ቆሮ. 1:18, ገላ. 6:14) +አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል:: የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ: የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ: #ኢየሱስ_ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ በወዴት አለና:: +ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን: እናመሰግነዋለን: እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት: ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን ተሻግረዋል:: +በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል:: ጠላትንም አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ ምስክርን አንፈልግም:: +"+ #በዓለ_መስቀል +"+ =>#መድኃኔ_ዓለም ክርስቶስ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ አይሁድ በአንድ ነገር ተቸገሩ:: የክርስቶስን ሐዋርያት እያሳደዱ ቢገድሉም ከመስቀሉና ሥጋ ክርስቶስ አርፎበት ከነበረው ጐልጐታ ላይ የሚደረገውን ተአምር ግን መግታት አልተቻላቸውም:: +መቼም ለተንኮል አያርፉምና ቅዱስ መስቀሉን ሽፍቶቹ ከተሰቀሉባቸው ጋር ደርበው አርቀው ቀበሩት:: አካባቢው የጉድፍ መጣያ እንዲሆንም አዋጅ ነገሩ:: ለክፋት ሲሆን ተባባሪው ብዙ ነውና ለ270 ዓመታት ያህል ቆሻሻ ቢጥሉበት ተራራ ሆነ:: +ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ እናታችን ቅድስት #እሌኒ (ሔለና) በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት: በቅዱስ #ኪራኮስ መሪነት: በቅዱስ #ሚካኤል ረዳትነት ደመራ አስደምራ: እጣን አጢሳ መካነ መስቀሉን አገኘች:: +መስከረም 17 ቀን የተጀመረው ቁፋሮ መጋቢት 10 ቀን ተጠናቆ: ንጹሕ መስቀሉ ወጥቶ ብርሃን በርቷል: ሙታን ተነስተዋል:: ከ10 ዓመት በሁዋላም የመስቀሉ ቤተ መቅደስ ታንጾ መስከረም 17 ቀን ተቀድሷል:: +ይህ ቅዱስ ዕፀ መስቀልም በደጉ #አፄ_ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን መጥቶ: በጻድቁ #አፄ_ዘርዓ_ያዕቆብ አማካኝነት በደብረ ከርቤ (#ግሸን_ማርያም) ተለብጦ ተቀምጧል:: =>አምላከ ቅዱሳን በኃይለ መስቀሉ: በሞገሰ መስቀሉ ይጠብቀን:: ከበረከቱ አሳትፎ በዓሉን የሰላም ያድርግልን =>+"+ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና . . . መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ:: የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ:: እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን:: +"+ (1ቆሮ. 1:18-23) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Sep 28, 2020Because queen Elani found the cross which jesus was nailed on
Sep 28, 2020