ከምወደው ፍቅረኛዬ እና የሴት ጓደኛዬ ጋር ተለያየሁ ፍቅረኛዬ የሚወደኝ ይመስለኝ ነበር ግን በቃ አልሆነምና ተለያየን የልብ ጓደኛዬም በብዙ ነገር ሳምናት እና ለሷ ብዙ ነገር ስሆንላት ባለባት ከባድ የቅናት መንፈስ ምክንያት ብዙ ነገሬን አበለሻሽታ ተጣላን(ከፍቅረኛዬ ጋር ማግጣ አይደለም) አሁን ላይ ሁለቱም ያደረጉኝን ነገር አእምሮዬ ሊረሳው አልቻለም በቃ እየተብሰለሰልኩ ነው ደሞም የምንሰራበት መስሪያ ቤት አንድ ነው ባየኋቸው ቁጥር በደላቸው ትዝ እያለኝ እበሳጫለሁ እንዴት ብዬ በደላቸውን ልርሳ መፍትሄ የምትሉትን እስቲ ምከሩኝ
Sep 09, 2022እንኳን አደረሰሽ። *ያፈቀሩትን ፍቅረኛ ያመኑትን ጓደኛ በተመሳሳይ ጊዜ ላይ ማጣት እጅግ ልብ ሰባሪ ነው። *እግዚአብሔር ግን ይወድሻል። በፍቅሩ አውሮሽ አለማፍቀሩን ማየት ተስኖሽ የነበርሽ አንቺን የፍቅረኛሽን ጭንብል ገፎ እውቱን እንድትረጂ ያደረገሽና ከቅናቷ የተነሳ ጓደኘነትን የመሰለ ሰማያዊ ክብርን ከሚያስገኝ ጥምረት በክፉ ቅናት የተነሳ ያጣችውን እህትሽን በሕይወትሽ ውስጥ በየትኛው ሁኔታ ልትጠነቀቂያት እንደሚገባ የገለጠለሽ አምላክ የጓደኛሽንም ሆነ የፍቅረኛሽን በደላቸውን በማሰብ ክፉን በክፉ እንድትቃወሚ ሳይሆን ይልቁንስ እነሱ አንቺን የሚያጸድቁሽ መሆናቸውን እንድትገነዘቢና ከቀደመው ይልቅ መልካም እንድትሆኚላቸውና በዚም የእሳትን ክምር በላያቸው ጭነሽ ወደ በጎው እንድትመሪያቸው ነውና በደላቸውን ከውለታ ቁጠሪው። #ሰዎች ላይዋጥላችኹ ይችላል ነገር ግን አስቡት ሰይጣን ባይኖር ክርስቶስን እንደምንወደው በምን እናረጋግጥ ነበር ? እኛ የመድኃኔዓለም መሆናችን የሚታወቀው የሰይጣንን ፍቃድ ስንቃወም አይደል ? ለዚኽ እኮ የሰይጣን መኖር አስፈላጊ ነው። #እናትዬ በሕይወታችን መልካም ከሚያደርጉልን ሰዎች በላይ የሚበድሉን ሰዎች ትልቅ ዋጋን ያስገኙናል። እነሱም ወደው ይኽን አያደርጉም ከኋላቸው ረቂቅ የሆነ ኃይል እየገፋቸው እንጂ። ስለነሱ መጸለይ ይገባናል። የቆምን የመሰለን እኛም እንዳንወድቅ ልንጠነቀቅ ይገባል። #ከቻልሽ ይኽን ለማድረግ ኃይልን እስክታገኝ ድረስ አተኩረሽ ፊታቸውን አትመልከች። ሌሎች ስሜቶች ወደአንቺ ቀርበው እንዳይረብሹሽ። በስራ ትተያያላችኹና ግን በተያያችኹበት ግዜ ኃዘንሽ በጭራሽ እንዲታይ አትፍቀጂ። ለማን አባቱ ብለሽ ? ደስተኛ መስለሽ ታዪ። የነሱ አንቺ ሕይወት ውስጥ መኖር አለመኖር ለውጥ እንደሌለው አሳያቸው። ትንሽ ግዜ ነው የሚከብድሽ ታሸንፊዋለሽ ይኽን ስሜት። በተቻለሽ አቅም ግን መልካም ሁኚላቸው። መልካም አዲስ ዐመት ይሁንልሽ።እኔ ባለፈው ዓመት ትምሕርትም መልካም ምኞትም የሚሆን አንድ ገጽ ጽሑፍ ነበር ጽፌ ለጠላቶቼ የሰጠዋቸው። አስበሽዋል ስንት ዓመት ልኖር እዚች ምድር ላይ ክፋታቸውን አስባለው ? እጅግ የመረረኝ ሰአት እጄን ዘርግቼ ኸረ ተው ፍረድልኝ 😂😂 እላለው እንደ ኃጢአቴ እንዳልፈረደብኝ ሳስብ ደግሞ ፍርዱን ትቼ ምሕረቱን እለምናለው። እግዚአብሔር ያውቃል በእውነትም ይፈርዳልና ለእግዚአብሔር ተይለት። መልካም አዲስ ዓመት ለሁላችኹም።
Sep 10, 2022