እንዴት ከረማችኹ ? እግዚአብሔር ይመስገን እኔ በጣም ደኽና ነኝ። እንደምወዳችኹ ደግሞ እግዚአብሔር ያውቃል። ለአንድ አንድ ነገር እንዲረዳኝ ጥያቄዬን በቅንነት መልሱ። #ለሴቶች 1.ለአቅመ ሔዋን ደርሰሻል ? በምን አወቅሽ ? የወር አበባ እና አካላዊ ለውጡን ወዲያ ትታችኁ ማለት ነው። 2.ሴትነት ላንቺ ምንድነው ? #ለወንዶች 1.ለአቅመ አዳም ደርሰሀል ? በምን አወቅክ ? አንተም አካላዊ ለውጡት ትተህ። 2.ወንድነት ላንተ ምንድነው ?. . . እንቀጥላለን። ስለእርዳታችኹ እግዜር ያክብርልኝ።
Sep 02, 2022እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነን እኛም 🙏 አቅመ-ሔዋንን ከተቀላቀልኩ ገና ቅርብ ጊዚዬ ነው, ከአካላዊ ለውጥ በተለየ መልኩ ለአቅመ-ሔዋን ደርሻለሁ ብዬ የማስበው 1, አስተሳሰቤ በፊት ከነበረኝ በጣም ተቀይሯል, በፊት እንደ ልጅ ብዙ አልጨነቅም አሁን ግን ወደፊት ከእኔ የምጠብቀውንም ሰው ከእኔ የሚጠብቀውንም እንዴት አድርጌ ማሳካት እንዳለብኝ ሁሌ አስባለሁ 2, ለነገሮች ቶሎ ምላሽ እሰጥ ነበር አሁን ግን በጣም ቀስ ብዬ መልስ የምሰጠው በንግግር ሳይሆን በተግባር 3, ሰው ስለኔ የሚሰጠው አስተያየት ያሳስበኝ ነበር አሁን ግን እየመረጥኩ ነው የምሰማው 2, ሴትነት ላወቀበት ክብር ነው, የተሰጠንን ነገር በአግባቡ እና በጊዜው ከተጠቀምንበት ትልቅ ስጦታ ነው አሜን 🙏, እግዚአብሔር ያክብርልን
Sep 03, 2022